አክስዮኖቻችሁን ማስመዝገብ ሲገባችሁ ላላስመዘገባችሁ አክስዮን ማህበራት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ እና ለህብረተሰቡ የተሰጠ ማሳሰቢያ

አክስዮኖቻችሁን ማስመዝገብ ሲገባችሁ ላላስመዘገባችሁ አክስዮን ማህበራት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ እና ለህብረተሰቡ የተሰጠ ማሳሰቢያ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የካፒታል ገበያውን ለመቆጣጠር በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 አንቀጽ 3 መሰረት የተቋቋመ ተቋም ሲሆን ባለስልጣኑ ከሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ አንዱም የሰነደ ሙአለ ንዋዮች ምዝገባ ነው፡፡ በአዋጅ ቁጥር 1248/2013 አንቀጽ 75 መሰረት ማንኛውም ለህዝብ የሚሸጥ ሰነደ ሙአለ ንዋይ ለሽያጭ ወይም […]

አስደሳች ዜና ለኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ!

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣንለአዋሽ ካፒታል አ.ማ. የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ በኢንቨስትመንት ባንክ (በባንክ ቡድን ውስጥ) ዘርፍ ሰጥቷል ። ይህ በገበያው ልማት ውስጥ ሌላው ቁልፍ ምዕራፍ ሲሆን፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉት የተፈቀደላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ጠቅላላ ቁጥር ወደ አስራ ሦስት (13) እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮች ጠቅላላ ቁጥር ወደ አራት (4) ከፍ አድርጓል። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር […]

ኢትዮጵያ በፋይናንሱ ዘርፍ ያላትን ምቹ  የኢንቨስትመንት እድል አስተዋወቀች

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር  ሀና ተኸልቁ በቻይና ሶስት ከተሞች ሻንጋይ፣ ሃርቢን እና ቾንግኪን  በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ በፋይናንሱ ዘርፍ በተለይም በካፒታል ገበያው ዙሪያ  እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን እና ሀገራችን ለቻይና ባለሀብቶች ያላትን ምቹ  ሁኔታ  እና ትልቅ አቅም አስተዋውቀዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሯ በቻይና ቆይታቸው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውጤታማ ውይይት  ያደረጉ ሲሆን  የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አቅምን ለማሳደግ […]

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን 18ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን አከበረ

ባለስልጣኑ በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ የሚገኘውን 18ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን  ከሰራተኞች  ጋር በመሆን የብሄራዊ መዝሙር በመዘመር እና በዓሉን በሚመለከት የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ ላይ  ውይይት በማድረግ አክብሯል፡፡ በውይይቱ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ክብር በአባቶቻቸን የተከፈለው ዋጋ ትልቅ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ቀጣይነት ባለው መልኩ የአሁኑ ትውልድም  የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ክብር ጠብቆ ማቆየት እንዲችል መስራት እንደሚገባም በውይይቱ ተነስቷል፡፡ የኢትዮጵያ የካፒታል […]

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በባህርዳር ያደረገው ውጤታማ ቆይታ

https://www.youtube.com/watch?v=AsJ3246KKp8 የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በባህርዳር ከተማ  በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አማካኝነት  በተዘጋጀው  የዳኞች ጉባኤ ላይ ተገኝቶ  በካፒታል ገበያ  በቂ ግንዛቤ  የሚያስጨብጥ  ውጤታማ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተሳታፊዎች  በተጨማሪም በአዲስ መልክ የተገነባውን  የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮን  የጎበኙበት ቆይታ ነበር፡፡ በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁን ጨምሮ […]

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የደም ልገሳ አደረገ

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች ጉባኤ በካፒታል ገበያ ዙሪያ ስልጠና የሰጠው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተሳታፊዎች ከጉባኤው ጎን ለጎን በደም ልገሳ መርሃ ግብር ተሳትፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁን ጨምሮ በህርዳር ከተማ ቆይታ ያደረጉ  የባለስልጣኑ ተሳታፊዎች የደም ልገሳ አድርገዋል፡፡ የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ  በህክምና ተቋማት ደም ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች በደም እጥረት የሚከሰት […]

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ጉባዔ በመገኘት የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር አካሄደ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች ጉባኤ ላይ በመገኘት ከተቋቋመ ጀምሮ ስላከናወናቸው ተግባራት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በባህርዳር ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር አካሂዷል ፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሩ የካፒታል ገበያ እና የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት እና የገበያ መሰረተ ልማቶች፣ ዳኞች እና እና ሌሎች የፍትህ ተቋማት […]

ትኩረት

የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንዶች ረቂቅ መመሪያ ህዝባዊ ምክክር መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ትምህርት ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 02፡30 እስከ ቀኑ 09፡30 እንደሚካሄድ ይታወቃል። በውይይት መድረኩ መሳተፍ የምትፈልጉ ቀጥሎ በተቀመጠው የመመዝገቢያ ቅጽ እስከ  መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ በአክብሮት እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የቴክኖሎጂ አማካሪ ቡድን በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አዳራሽ የጋራ ውይይት አካሄዱ፡፡

ሰኔ 27/ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (የኢካገባ)  የውይይቱ  ዋና አላማ   ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች  እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መንግስት ያወጣቸውን መመሪያዎች መነሻ በማድረግ በጋራ መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት  ያደረገ  ነበር፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ ካፒታል ገብያ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች እና ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ በሚደረግባቸው ጉዳዮች እንዲሁም የተሳለጠ […]