የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ባለስልጣኑ) የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ ተቀጥላ ኩባንያ (Subsidiary) ለሆነው ዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ሰጥቷል። ይህም ተቋሙን በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጥላ ኩባንያ በማቋቋም እንዲንቀሳቀስ ፈቃድ የተሰጠው የመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ያደርገዋል። የተሰጠው ፈቃድ ድርጅቱ በኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ ስር እንዲሠራ የሚፈቅድ ሲሆን፤ ባለስልጣኑ ከዚህ በተጨማሪ የአምስት (5) የቦርድ […]