ECMA Gold

ሚዲያ

ገበያን የሚዘውሩ ሴቶች  በሚል መሪ ቃል ለአንድ ቀን ከግማሽ የተካሄደው ሲምፖዚየም ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ የንግድና የፋይናንስ ዘርፍ ሴት መሪዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ ባለሙያዎች እና የተለያዩ አካላት ተሳትፈውበት በስኬት  ተጠናቋል። ሲምፖዚየሙ የካፒታል ገበያ መሰረታዊ ሐሳቦችን፣ የገበያውን ሥነ-ምህዳር እና የቁጥጥር ማዕቀፍ፣ የካፒታል ገበያ መሣሪያዎችን፣ እንዲሁም መሰረታዊ የካፒታል ገበያ ግንዛቤዎችን ያስጨበጡ የተለያዩ ስልጠናዎች የተሰጡበት ሲሆን ተግባራዊ የፓናል ውይይቶችና የልምድ […]

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭዎች  ከምዝገባ በኋላ ስለሚጠበቅባቸው ግዴታዎች ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ከምዝገባ በኋላ ስለሚጠበቁ መረጃን ይፋ የማድረግ የህግ ግዴታዎች ላይ በሚመለከት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሲሆን ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2017 እና ከምዝገባ በኋላ ስለሚጠበቁ ጉዳዮች በተመለከተ ትኩረት አድርጓል፡ ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2017 አንቀጽ […]

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባለፈው የበጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን ለመገምገም እና  ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ፈቃድ ከተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ባንኮች እና የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አከናዋዮች ጋር በዛሬው ዕለት የጋራ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ተገኝቷል፡፡ በውይይቱ ባለፈው የበጀት አመት በፈቃድ አሰጣጥ፣ በቁጥጥር እና የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ምዝገባ አፈፃፀም ላይ ባለስልጣኑ ያከናወናቸው ተግባራት አና ዋና ዋና ስኬቶች የቀረቡ ሲሆን ስኬቶችን በማስቀጠል እና […]

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ  ባለሥልጣን የ2018 የሰመር ካምፕ ተስታፊዎች  እና  የበይነ መርብ ስልጠና ሲወሰዱ የነበሩ ሰልጣኞች የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡ የሰመር ካሞፕ ሰልጣኞች ለሁለት ሳምንታት በተለያዩ የካፒታል ገበያ ርዕሰ ጉዳዮች እንዲሁም በበይነ መርብ ለ12 ተከታታይ ሳምንታት ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ናቸው፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁ  የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ሰልጣኞች በቆይታቸው […]