ECMA Gold

ECMA / ኢካገባ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሉክሰምበርግ ልዑካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ የሉክስምበርግ አምባሳደር ከሆኑት  ክቡርት ዣን ክራውዘር፣ ሻርዠ ደፌር   አሪያን ሞያ እንዲሁም የመጀመሪያ ጸሀፊ ከሆኑት ማክስም ላድሪየርን ጋር በሉክሰምበርግ እና በኢትዮጵያ መካከል በካፒታል ገበያ  ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ውጤታማ ውይይት አድርጓል።

ውይይቱ ቀደም ሲል የነበሩ ግንኙነቶችን መሰረት አድርጎ የቀጠለ ሲሆን በኢትዮጵያ የሉክሰምበርግ ኢምባሲ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ልማት ሥራዎች ለመደገፍ በሚችላቸው የቴክኒክ ድጋፍ እና የትብብር መስኮች ላይም ትኩረት ሰጥቷል፡፡

በውይይቱ ከሉክሰምበርግ ስቶክ ኤክስቸንጅ (Luxembourg Stock Exchange) እና በሉክሰምበርግ መንግሥት ከሚደገፈው የፋይናንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ማዕከል (Luxembourg House of Financial Technology) ጋር በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡

በዚህም የእውቀት ሽግግር፣ የአቅም ግንባታ፣ የገበያ ልማት እና በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር ውስጥ ውስጥ በጋራ የሚስሩ የትብብር መስኮችን በመለየት እነዚህን የትብብር ዕድሎች በተግባር ለማዋል እና ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ዕድገት መጠናከር አጋርነትን በማሳደግ ረገድ በኢትዮጵያ የሉክስምበርግ ኢምባሲ እያደረገ ላለው እገዛ እንዲሁም ለአምባሳደር ዣን ክራውዘር እና ለባለደረቦቿ ያለውን ምስጋና ይገልጻል።