ECMA Gold

ECMA / ኢካገባ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የእቅድ አፈጻጸም ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን የገመገመበት እና የ2019 በጀት ዓመት ስትራቴጂካዊ እቅድን የተመለከተበት ውይይት አድርጓል፡፡
 
መድረኩ ባለስልጣኑ ባለፈው የበጀት ዓመት የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ለማሳደግ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት፣ የተመዘገቡ ስኬቶች እና ቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ገንቢ ውይይት የተካሄደበት ነው፡፡
 
በዉይይቱ በተለይም የቁጥጥር ሥርዓቱን በማጠናከር፣ የዲጂታል አሰራር ትራንስፎርሜሽንን በማፋጠን፣ የካፒታል ገበያ ተሳታፊዎችን በማሳደግ እንዲሁም የኢንቨስተሮች ትምህርትና ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮችን በማስፋት ረገድ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውም ቀርቧል፡፡
 
ባለስልጣኑ ተቋማዊ አቅምን በማሳደግ እና የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ዕድገት ለማፋጠን ያለውን ቁርጠኝነት የሚቀጥል ሲሆን በ2019 በጀት ዓመት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ስትራቴጂካዊ ተግባራት ቀርበውም ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
 
ከውይይቱ በተጨማሪም የባለስልጣኑ ሰራተኞች ቤተሰብነታቸውን የሚያጠናክሩበት የተለያዩ አዝናኝ ጨዋታዎች እና የቡድን እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል፡፡