የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭዎች ከምዝገባ በኋላ ስለሚጠበቅባቸው ግዴታዎች ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ከምዝገባ በኋላ ስለሚጠበቁ መረጃን ይፋ የማድረግ የህግ ግዴታዎች ላይ በሚመለከት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሲሆን ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2017 እና ከምዝገባ በኋላ ስለሚጠበቁ ጉዳዮች በተመለከተ ትኩረት አድርጓል፡
ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2017 አንቀጽ 135 መሠረት ለሕዝብ ሽያጭ የቀረቡ ወይም በሕዝብ የተያዙ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች አውጪ በቋሚነት መረጃን ለህዝብ ይፋ የማድረግ የህግ ግዴታ ያለበት ሲሆን እነዚህን የህግ ግዴታዎች በወቅቱና በተገቢው መልኩ መወጣት እንደሚያስፈልግም በስልጠናው ተገልጿል፡፡
ስልጠናው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭዎች ከምዝገባ በኋላ የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት በተመለከተ ያላቸውን ግንዛቤ ማጠናከር ያለመ ሲሆን በኢትዮጵያ እያደገ ባለው የካፒታል ገበያ ውስጥ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን ያስችላል።