የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የ2018 የሰመር ካምፕ ተስታፊዎች እና የበይነ መርብ ስልጠና ሲወሰዱ የነበሩ ሰልጣኞች የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡
የሰመር ካሞፕ ሰልጣኞች ለሁለት ሳምንታት በተለያዩ የካፒታል ገበያ ርዕሰ ጉዳዮች እንዲሁም በበይነ መርብ ለ12 ተከታታይ ሳምንታት ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ናቸው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ሰልጣኞች በቆይታቸው የቀሰሙትን እውቀት እና ያገኙትን ግንዛቤ በመጠቀም በማደግ ላይ ባለው የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
መርሃ ግብሩ ተሳታፊዎችን ወደ ላቀ የፋይናንስ እውቀት፣ ግንዛቤ እና ትርጉም ያለው የካፒታል ገበያ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እድል የሚከፍት ሲሆን ለሁሉም ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት እና በከፈተኛ ውጤት ላጠናቀቁ የትምህርት እድል ተመቻችቶላቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የካፒታል ገበያ ግንዛቤ ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡