ECMA Gold

ECMA / ኢካገባ

የካፒታል ገበያ ኢንቬስተሮች ቀን አውደ ርዕይ በስኬት ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ የካፒታል  ባለስልጣን ከሰኔ 12 እስከ13 2018 ዓ.ም ያካሄደውን የሁለት ቀናት  የኢንቬስተሮች አውደ ርዕይ በስኬት አጠናቋል።

በአውደ ርዕዩ  ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጎብኚዎች  የጎበኙ ሲሆን፥ ስለ ካፒታል ገበያው እድሎች እና  የኢንቨስትመንት አማራጮች ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠበት መርሃ -ግብር  ሆኖ አልፏል።

ለአወደ ርዕዩ  ውጤታማ መሆን እና ለስኬታማነቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት፣  ለተሳታፊዎች እና ለጉብኝዎች  በሙሉ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን  ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል ።

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ  ባለስልጣን  የካፒታል ገበያውን ግንዛቤ የሚያስጨብጡ፣  በመላው ኢትዮጵያ የኢንቬስተሮችን  ደህንነት የሚያስጠብቁ መሰል መድረኮችን በማዘጋጀት በቂ ግንዛቤ እንዲኖር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡