ECMA Gold

ሚዲያ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሰፊ የፈቃድ ማመልከቻ ግምገማ ሂደት በኋላ ለኤ ኤም ጂ ኢንቨስትመንት ባንክ ኃላ/የተ/የግ/ማ እና ለ ናይልብሪጅ ኢንቨስትመንት ባንክ ኃላ/የተ/የግ/ማ የኢንቨስትመንት ባንክነት ፈቃድ መስጠቱን በደስታ ይገልጻል። በተጨማሪም ባለስልጣኑ የሁለቱን አዳዲስ ኢንቨስትመንት ባንኮች ስምንት (8) ተሿሚ እንደራሴዎች እና የአሥር (10) ቦርድ አባላት ሹመትን አጽድቋል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ዳግማዊት ሽፈራው ፈቃዱን ህዳር 4 ቀን […]

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ  ባለስልጣን በረቂቅ የውጭ ፖርትፎሊዮ ኢንቨስትመንት መመሪያ ላይ ከባለድርሻ አካላት እና  ከተለያዩ ተሳታፊዎች ጋር   ባለስልጣኑ ባዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ዙሪያ ህዝባዊ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ተሳታፊዎች በረቂቅ መመሪያው ይዘቶች ላይ  ያላቸውን ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች እና ሀሳቦችን ያነሱ ሲሆን የውጭ ፖርትፎሊዮ  ኢንቨስትመንት ረቂቅ መመሪያ ስለያዛቸው ዋና ዋና ነጥቦች ገለጻ ከተደረገ በኋላ የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በተሳታፊዎች […]

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ወ/ሪት ሀና ተኸልቁ አዲስ ለተሾሙት ዋና ዳይሬክተር ዳግማዊት ሽፈራው የስራ ርክክብ በዛሬው እለት ያደረጉ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ለአዲሷ ዋና ዳይሬክተር ዳግማዊት ሽፈራው እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርም አቀባበል ተደርጓል። አዲስ የተሾሙት ዋና ዳይሬክተር ዳግማዊት ሽፈራው ለቀድሞዋ ዋና ዳይሬክተር እና ለአሁኗ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀና ተኸልቁ በባለስልጣኑ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን […]

https://www.youtube.com/watch?v=0ihoAhmNGyMየኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በባሕርዳር ከተማ ለሁለት ቀናት የቆየ የተሳካ የካፒታል ገበያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡ በባህርዳር ከተማ ለሁለት ቀናት የተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በመጀመሪያ  ለአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች የተሰጠ ሲሆን በሁለተኛ ቀን መርሃ ግብሩ ደግሞ ለባሕርዳር ከተማ የንግዱ ማህበርሰብ እና የባሕርዳር ዩኒቨርስቲ መምህራን እና ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር እንዲሳካ ላደረጉት […]

Title
Press Release November 25, 2024