ECMA Gold

ECMA / ኢካገባ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አዲስ ለተሾሙት አመራሮች አቀባበል አደረገ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ወ/ሪት ሀና ተኸልቁ አዲስ ለተሾሙት ዋና ዳይሬክተር ዳግማዊት ሽፈራው የስራ ርክክብ በዛሬው እለት ያደረጉ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ለአዲሷ ዋና ዳይሬክተር ዳግማዊት ሽፈራው እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርም አቀባበል ተደርጓል።

አዲስ የተሾሙት ዋና ዳይሬክተር ዳግማዊት ሽፈራው ለቀድሞዋ ዋና ዳይሬክተር እና ለአሁኗ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀና ተኸልቁ በባለስልጣኑ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ዕድገት ለማፋጠን ከባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ተቋማዊ ተልዕኮውን ለማጠናከር እንዲሁም ግልጽ፣ አካታች እና ጠንካራ የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ ይቀጥላል።