የሴቶችን ተሳትፎ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ማጠናከር ያለመው ሲምፓዚየም በስኬት ተጠናቀቀ

ገበያን የሚዘውሩ ሴቶች በሚል መሪ ቃል ለአንድ ቀን ከግማሽ የተካሄደው ሲምፖዚየም ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ የንግድና የፋይናንስ ዘርፍ ሴት መሪዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ ባለሙያዎች እና የተለያዩ አካላት ተሳትፈውበት በስኬት ተጠናቋል። ሲምፖዚየሙ የካፒታል ገበያ መሰረታዊ ሐሳቦችን፣ የገበያውን ሥነ-ምህዳር እና የቁጥጥር ማዕቀፍ፣ የካፒታል ገበያ መሣሪያዎችን፣ እንዲሁም መሰረታዊ የካፒታል ገበያ ግንዛቤዎችን ያስጨበጡ የተለያዩ ስልጠናዎች የተሰጡበት ሲሆን ተግባራዊ የፓናል ውይይቶችና የልምድ […]
ሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭዎች ከምዝገባ በኋላ ስለሚጠበቅባቸው ግዴታዎች የሚያስገነዝብ ስልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭዎች ከምዝገባ በኋላ ስለሚጠበቅባቸው ግዴታዎች ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ከምዝገባ በኋላ ስለሚጠበቁ መረጃን ይፋ የማድረግ የህግ ግዴታዎች ላይ በሚመለከት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሲሆን ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2017 እና ከምዝገባ በኋላ ስለሚጠበቁ ጉዳዮች በተመለከተ ትኩረት አድርጓል፡ ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2017 አንቀጽ […]
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከካፒታል ገበያ ተዋናዮች ጋር እየተወያየ ነው

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባለፈው የበጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን ለመገምገም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ፈቃድ ከተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ባንኮች እና የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አከናዋዮች ጋር በዛሬው ዕለት የጋራ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ተገኝቷል፡፡ በውይይቱ ባለፈው የበጀት አመት በፈቃድ አሰጣጥ፣ በቁጥጥር እና የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ምዝገባ አፈፃፀም ላይ ባለስልጣኑ ያከናወናቸው ተግባራት አና ዋና ዋና ስኬቶች የቀረቡ ሲሆን ስኬቶችን በማስቀጠል እና […]
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሰመር ካምፕ እና የበይነ መርብ የስልጠና መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ መድረክ አካሄደ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የ2018 የሰመር ካምፕ ተስታፊዎች እና የበይነ መርብ ስልጠና ሲወሰዱ የነበሩ ሰልጣኞች የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡ የሰመር ካሞፕ ሰልጣኞች ለሁለት ሳምንታት በተለያዩ የካፒታል ገበያ ርዕሰ ጉዳዮች እንዲሁም በበይነ መርብ ለ12 ተከታታይ ሳምንታት ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ናቸው፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ሰልጣኞች በቆይታቸው […]
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የእቅድ አፈጻጸም ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን የገመገመበት እና የ2019 በጀት ዓመት ስትራቴጂካዊ እቅድን የተመለከተበት ውይይት አድርጓል፡፡ መድረኩ ባለስልጣኑ ባለፈው የበጀት ዓመት የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ለማሳደግ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት፣ የተመዘገቡ ስኬቶች እና ቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ገንቢ ውይይት የተካሄደበት ነው፡፡ በዉይይቱ በተለይም የቁጥጥር ሥርዓቱን በማጠናከር፣ የዲጂታል አሰራር ትራንስፎርሜሽንን በማፋጠን፣ የካፒታል ገበያ ተሳታፊዎችን በማሳደግ እንዲሁም የኢንቨስተሮች […]
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለሦስት አዲስ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፈቃድ ሰጠ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሰፊ የፈቃድ ማመልከቻ ግምገማ ሂደት በኋላ ለሦስት (3) አዳዲስ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፍቃድ በመስጠቱ የተሰማውን ደስታ ይገልጻል። በተጨማሪም ባለስልጣኑ የሦስቱን አዳዲስ አገልግሎት ሰጭዎች አስር (10) ተሿሚ እንደራሴዎችን ፈቃድ ያጸደቀ ሲሆን፣ የ አስራ አምስት (15) ቦርድ አባላት ሹመትንም አጽድቋል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ሃና ተኸልቁ ፈቃዱን ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. […]
የካፒታል ገበያ ኢንቬስተሮች ቀን አውደ ርዕይ በስኬት ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ የካፒታል ባለስልጣን ከሰኔ 12 እስከ13 2018 ዓ.ም ያካሄደውን የሁለት ቀናት የኢንቬስተሮች አውደ ርዕይ በስኬት አጠናቋል። በአውደ ርዕዩ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጎብኚዎች የጎበኙ ሲሆን፥ ስለ ካፒታል ገበያው እድሎች እና የኢንቨስትመንት አማራጮች ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠበት መርሃ -ግብር ሆኖ አልፏል።ለአወደ ርዕዩ ውጤታማ መሆን እና ለስኬታማነቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት፣ ለተሳታፊዎች እና ለጉብኝዎች በሙሉ የኢትዮጵያ […]
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሉክሰምበርግ ልዑካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ የሉክስምበርግ አምባሳደር ከሆኑት ክቡርት ዣን ክራውዘር፣ ሻርዠ ደፌር አሪያን ሞያ እንዲሁም የመጀመሪያ ጸሀፊ ከሆኑት ማክስም ላድሪየርን ጋር በሉክሰምበርግ እና በኢትዮጵያ መካከል በካፒታል ገበያ ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ውጤታማ ውይይት አድርጓል።ውይይቱ ቀደም ሲል የነበሩ ግንኙነቶችን መሰረት አድርጎ የቀጠለ ሲሆን በኢትዮጵያ የሉክሰምበርግ ኢምባሲ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ልማት ሥራዎች ለመደገፍ በሚችላቸው የቴክኒክ ድጋፍ […]
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ባለስልጣኑ) የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ ተቀጥላ ኩባንያ (Subsidiary) ለሆነው ዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ሰጥቷል። ይህም ተቋሙን በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጥላ ኩባንያ በማቋቋም እንዲንቀሳቀስ ፈቃድ የተሰጠው የመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ያደርገዋል። የተሰጠው ፈቃድ ድርጅቱ በኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ ስር እንዲሠራ የሚፈቅድ ሲሆን፤ ባለስልጣኑ ከዚህ በተጨማሪ የአምስት (5) የቦርድ […]
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ሶቨሬን ፈንድ ጋር ተወያየ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ሶቨሬን ፈንድ ጋር ተወያየ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ሶቨሬን ፈንድ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ፈንዱ በካፒታል ገበያው ስለሚሳተፍበት ሁኔታ ውይይት አደረገ፡፡ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ በውይይቱ እንደገለጹት ፈንዱ በተለያዩ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ያለውን አቅም ወደ ካፒታል ገበያው በማምጣት ተቋማዊ ዕድገቱን ከመገንባት ባለፈ ለሀገራዊው ገበያ መጠናከር ወሳኝ ሚና […]