ECMA Gold

ECMA / ኢካገባ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ሶቨሬን ፈንድ ጋር ተወያየ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ሶቨሬን ፈንድ ጋር ተወያየ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ሶቨሬን ፈንድ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ፈንዱ በካፒታል ገበያው ስለሚሳተፍበት ሁኔታ ውይይት አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ በውይይቱ እንደገለጹት ፈንዱ በተለያዩ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ያለውን አቅም ወደ ካፒታል ገበያው በማምጣት ተቋማዊ ዕድገቱን ከመገንባት ባለፈ ለሀገራዊው ገበያ መጠናከር ወሳኝ ሚና መጫወት እንደሚችል ገልጸዋል።

በተለይም በፈንዱ ሥር የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ወደ ሕዝብ ኩባንያነት በመቀየር አክሲዮኖችን ወይም የዕዳ ሰነዶችን ለገበያ በማውጣት ለፕሮጀክቶቻቸው ማስፈጸሚያ የሚሆን የረጅም ጊዜ ፋይናንስ ማግኘት ስለሚችሉበት፣ እንዲሁም ተቋሙ ያለውን ሀብት በሌሎች አስተማማኝ የሰነደ-ሙዓለ ነዋይ አማራጮች ላይ እንደ ተቋማዊ ኢንቨስተር የገቢ ምንጩን ስለሚያሰፋበት ሁኔታ ውጤታማ ምክክር ተደርጓል።