ECMA Gold

ECMA / ኢካገባ

የሴቶችን ተሳትፎ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ማጠናከር ያለመው ሲምፓዚየም በስኬት ተጠናቀቀ

ገበያን የሚዘውሩ ሴቶች  በሚል መሪ ቃል ለአንድ ቀን ከግማሽ የተካሄደው ሲምፖዚየም ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ የንግድና የፋይናንስ ዘርፍ ሴት መሪዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ ባለሙያዎች እና የተለያዩ አካላት ተሳትፈውበት በስኬት  ተጠናቋል።

ሲምፖዚየሙ የካፒታል ገበያ መሰረታዊ ሐሳቦችን፣ የገበያውን ሥነ-ምህዳር እና የቁጥጥር ማዕቀፍ፣ የካፒታል ገበያ መሣሪያዎችን፣ እንዲሁም መሰረታዊ የካፒታል ገበያ ግንዛቤዎችን ያስጨበጡ የተለያዩ ስልጠናዎች የተሰጡበት ሲሆን ተግባራዊ የፓናል ውይይቶችና የልምድ ልውውጦችም ተከናውነውበታል፡፡

ይህ ሲምፓዚየም የካፒታል ገበያን ግንዛቤ ለማዳበር እና በማደግ ላይ ባለው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር የሚረዱ መንገዶችን ለመዳሰስ መልካም አጋጣሚን ፈጥሯል።