ECMA / ኢካገባ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በባህርዳር ያደረገው ውጤታማ ቆይታ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በባህርዳር ከተማ  በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አማካኝነት  በተዘጋጀው  የዳኞች ጉባኤ ላይ ተገኝቶ  በካፒታል ገበያ  በቂ ግንዛቤ  የሚያስጨብጥ  ውጤታማ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተሳታፊዎች  በተጨማሪም በአዲስ መልክ የተገነባውን  የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮን  የጎበኙበት ቆይታ ነበር፡፡

በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁን ጨምሮ የጉባኤው ተሳታፊዎች ደም በመለገስ  እጅግ ውጤታማ   ቆይታ የነበራቸው ሲሆን መድረኩ በካፒታል ገበያ ህጎች እና መመሪያዎች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ መስጠት የተቻለበት ነበር፡፡

✅ የባህርዳር ቆይታችንን በሚመለከት የተዘጋጀውን አጭር ምስል ይመልከቱ