ECMA Gold

ECMA / ኢካገባ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በባሕርዳር ከተማ ለሁለት ቀናት የቆየ የተሳካ የካፒታል ገበያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በባሕርዳር ከተማ ለሁለት ቀናት የቆየ የተሳካ የካፒታል ገበያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

በባህርዳር ከተማ ለሁለት ቀናት የተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በመጀመሪያ  ለአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች የተሰጠ ሲሆን በሁለተኛ ቀን መርሃ ግብሩ ደግሞ ለባሕርዳር ከተማ የንግዱ ማህበርሰብ እና የባሕርዳር ዩኒቨርስቲ መምህራን እና ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡

ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር እንዲሳካ ላደረጉት  የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የአማራ ክልል ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እንዲሁም የባህርዳር ዩኒቨርስቲን ባለስልጣኑ ያመሰግናል፡፡

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በባህርዳር ከተማ የነበረውን ቆይታ በሚመለከት የተዘጋጀውን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡