የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ከሰራተኞቹ ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁ ባለፉት ስድስት ወራት ተቋሙ ተጨባጭ የሆኑ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ እንደጠቀሱት በተለይም የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፍቃድ ቁጥር መጨመሩን ፣የተለያዩ አክሲዮን ማህበራት የሰነደ ሙዓለንዋዮች ምዝገባ መከናወኑን እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች የካፒታል ገበያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በስኬት መከናወናቸውን አንስተዋል።
በተጨማሪም ባለስልጣኑ ሁለተኛውን ቀጣናዊ የካፒታል ገበያ ጉባኤ በስኬት ማጠናቀቁን የጠቀሱ ሲሆን በቀጣይ ወራትም የተጀመሩ ተግባራትን በላቀ ውጤታማነት ለመፈጸም የላቀ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ከእቅድ ግምገማው በተጨማሪም የባለስልጣኑ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የአሁኑ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ኢሳያስ ካሳ ለሰራተኞቹ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም የቡድን ሥራን ለማበረታታት እንዲሁም በሠራተኞች መካከል አንድነትን ለመፍጠር የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች እና የመዝናኛ መርሐ-ግብሮች ተከናውነዋል፡፡