
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች ጉባኤ በካፒታል ገበያ ዙሪያ ስልጠና የሰጠው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተሳታፊዎች ከጉባኤው ጎን ለጎን በደም ልገሳ መርሃ ግብር ተሳትፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁን ጨምሮ በህርዳር ከተማ ቆይታ ያደረጉ የባለስልጣኑ ተሳታፊዎች የደም ልገሳ አድርገዋል፡፡
የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ በህክምና ተቋማት ደም ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች በደም እጥረት የሚከሰት የህይወት ማጣትን የሚታደግ በመሆኑ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በዚህ የደም ልገሳ መርሃ ግብር በመሳተፉ የተሰማውን ደስታ ይገልጻል፡፡
