ECMA / ኢካገባ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የቴክኖሎጂ አማካሪ ቡድን በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አዳራሽ የጋራ ውይይት አካሄዱ፡፡

ECMA Ethiopian AI Institute and PMO Advisor Discuss Support for Startups and SMEs 1

ሰኔ 27/ 2017 .

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (የኢካገባ)

 የውይይቱ  ዋና አላማ   ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች  እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መንግስት ያወጣቸውን መመሪያዎች መነሻ በማድረግ በጋራ መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት  ያደረገ  ነበር፡፡

በተለይም የኢትዮጵያ ካፒታል ገብያ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች እና ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ በሚደረግባቸው ጉዳዮች እንዲሁም የተሳለጠ የቁጥጥር ሁኔታን ለመፍጠር የሚያስችሉ ስልቶችን ለመቀየስ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ECMA Ethiopian AI Institute and PMO Advisor Discuss Support for Startups and SMEs 2

በአጠቃላይ  በተቋማቱ የተካሄደው ዉይይት በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጅ እና በፓሊሲ ጉዳዮች ተቀናጅቶ በመስራት በሀገራችን ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖር ያለው  ሚና የላቀ ነው ፡፡

በውይይቱ ከዚህ  በተጨማሪም  በቀጣይነት በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ከቁጥጥር ድጋፍ እንዲሁም በአጠቃላይ ከካፒታል ገብያ ጋር በተያያዙ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡