የኢ.ካ.ገ.ባ በአዋጅ ቁጥር 1248/2013 የተሰጡ የተለያዩ የማስፈጸም ስልጣኖችን ይዟል። ዳይሬክቶሬቱ በኢ.ካ.ገ.ባ ቁጥጥር ስር ባሉ ግለሰቦች ወይም ህጋዊ ሰውነት ባላቸው አካላት ሊፈጸሙ የሚችሉ የካፒታል ገበያ ህጎች እና መመሪያዎች ጥሰቶችን የማጣራት ኃላፊነት ተሰጥቶታል።
ይህ ኃላፊነት ፈቃድ የተሰጣቸውን አገልግሎት ሰጪዎች እንቅስቃሴ መገምገም እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለህግ ተገዥ አልሆኑም ተብለው የተጠረጠሩትን የመመርመር፣ የምግባር ጉድለት፣ ገበያን አላግባብ መጠቀም ወይም ሌሎች ባለስልጣኑ በበላይነት ምልከታ የሚያደርግባቸው ህጎች ሲጣሱ ምርመራ ማድረግን ያጠቃልላል። በምርመራ ወቅት ዳይሬክቶሬቱ እንደ ገበያን ያለ አግባብ መጠቀም፣ የገበያ ሽፍጥ የመሳሰሉ የካፒታል ገበያ ወንጀሎችን ወይም ሌሎች ፈቃድ ያላቸው ወይም ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦችን የሚያካትቱ ህገወጥ ተግባራትን የያዙ ማስረጃዎችን ሊያገኝ ወይም ጥርጣሬዎች ሊኖሩት ይችላል። እንደዚህ አይነት ግኝቶችም ፍትህ ሚኒስቴር እና የፌዴራል ፖሊስን ጨምሮ አግባብነት ላላቸው የህግ አስፈፃሚ አካላት ሪፖርት ይደረጋሉ።
የምርመራ እና ህግን የማስፈጸም ዳይሬክቶሬት ግኝቶቹን ለኢ.ካ.ገ.ባ ውሳኔ ሰጭ አካል ሪፖርት ያደርጋል እንዲሁም፤ ለመፍትሄ እርምጃዎች እና/ወይም ተገቢውን የህግ ማስፈጸሚያ እርምጃለመውሰድ የሚረዱ ምክሮችን ያቀርባል። ከዚሀ በተጨማሪ የህግ ማስፈጸሚያ ውሳኔዎችን ውጤት የመተግበር እና የመከታተል ሃላፊነትም አለበት።
It is to be recalled that the public consultation on the Draft Directive on Collective Investment Schemes (CIS) will be held on September 16, 2025, at Addis Ababa University, Commerce Campus Hall, from 08:30 AM to 03:30 PM. Those interested in attending are kindly requested to register below.
Be part of a groundbreaking event where industry leaders and experts will gather to explore the future of capital markets. Don’t miss your chance to connect, learn, and engage with key players in the industry. Reserve your spot now!