የብቃት መስፈርቶች

የብቃት መስፈርቶች

በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ቁጥጥር ሳንድቦክስ ውስጥ መሳተፍ ከሳንድቦክሱ ዓላማዎች እና የቁጥጥር ማዕቀፎች ጋር መጣጣምን የሚያረጋግጡ ልዩ መስፈርቶችን በማሟላት ላይ የተመሠረተ ነው። የብቃት መመዘኛችን የተነደፈው የሳንድቦክሱን ልዩ አካባቢ ለመጠቀም የተዘጋጁ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ዝግመተለውጥ/እድገት ላይ አስተዋፅዖ ማድረግ የሚችሉ ድርጅቶችን ለመለየት ነው። የሚከተሉት መመዘኛዎች በሁሉም አመልካቾች መሟላት አለባቸው።

የታቀደው የካፒታል ገበያ አገልግሎት፣ ምርት ወይም ቴክኖሎጂ በካፒታል ገበያ ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ፍላጎቶችን በማስተናገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሸማቾችን፣ ተቆጣጣሪዎችን፣ ባለሀብቶችን ወይም አገልግሎት ሰጪዎችን በቀጥታ የሚጠቅም መሆን አለበት። ይህም የፋይናንስ አቅርቦትን እና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል፣ የገበያ ቅልጥፍናን ለመጨመር ወይም ሌሎች ሊለኩ የሚችሉ ጥቅሞችን ለአገሪቱ ሸማቾች ለማቅረብ ያለሙ ፈጠራዎችን ያካትታል።

አመልካቾች አገልግሎታቸው፣ ምርታቸው ወይም ቴክኖሎጂያቸው በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ላይ ያሉ አዳዲስ ወይም ነባር መፍትሄዎች ያቀርባሉ ተብሎ ከሚጠበቀው በተለየ መልኩ እንደሚቀርብ ማሳየት አለባቸው። ፈጠራው የፋይናንሺያል መልክዓ ምድሩን የመቀየር አቅም ያላቸውን አዳዲስ አቀራረቦችን ወይም ቴክኖሎጂዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማስተዋወቅ ይኖርበታል።

የታቀደው መፍትሔ/አቅርቦት ለተጠቃሚዎች የሚሰጠውን ጥቅም በግልፅ ማስቀመጥ አለበት፣ እነዚህም በደህንነት፣ በተጠቃሚ ልምድ፣ በዋጋ ቅነሳ ወይም በአገልግሎቶች ተደራሽነት ላይ ያሉ ማሻሻያዎችን ሊያካትት ይችላል። ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወሳኝ ለሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እና ጀማሪ ገበያዎች የፋይናንስ ተደራሽነትን የሚያሰፉ መፍትሄዎች ላይ ልዩ ትኩረት ይደረጋል።

ማመልከቻው የታሰበውን ፈጠራ ለመፈተሽ/ለመሞከር የሳንድቦክሱ አካባቢ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ አለበት። ይህ የቁጥጥር ተለዋዋጭነት አስፈላጊነትን፣ ስለ ምርቱ/ፈጠራው ስራ ካይ ካሉ ህጎች ጋር ስላለው መስተጋብር የመማር እድል እና ከECMA የቅርብ ምክር የማግኘትን ጥቅሞችን ያካትታል።

ድርጅቱ ወደ ሳንድቦክሱ ከገባ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከእውነተኛ ደንበኞች ጋር በቀጥታ በገበያ አካባቢው ሙከራን የመጀመር ዝግጁነቱን ማሳየት አለበት። ይህም የዳበረ/የበለጸገ ምርት/አቅርቦት ወይም አገልግሎት፣ አስፈላጊው ቴክኒካል እና ኦፕሬሽን መሠረተ ልማት እና ተሳታፊዎችን ለመጠበቅ የተሟሉ እርምጃዎች መኖራቸውን ያካትታል። አመልካቾች ዝቅተኛ አዋጭ ምርታቸውን (MVP)፣ የሸማቾች ጥበቃን ለማረጋገጥ የተነደፉ ቁልፍ ፖሊሲዎች እና አካሄዶች፣ የተቋቋሙ አጋርነቶች/ሽርክናዎች፣ ሙከራውን ለማካሄድ በቂ ግብአቶች፣ የደንበኞች ተሳትፎ እና የኦንቦርዲንግ ሂደቶች እና የንግድ ምዝገባ ትክክለኛ የምስክር ወረቀት በማቅረብ ለታቀደው ሙከራ ዝግጁነታቸውን እንዲያሳዩ ይጠየቃሉ።

ሳንድቦክሱ ቁጥጥር በሚደረግበት መልኩ የቁጥጥር እፎይታን የሚሰጥ ቢሆንም፣ ሁሉም ተሳታፊዎች በሳንድቦክሱ ሙከራ ግዜ የማይታለፉ የሕግ እና የቁጥጥር ደረጃዎችን መከተል አለባቸው። ይከውም የሙከራ እንቅስቃሴዎች የሰፊውን የፋይናንስ ሥርዓት ተዓማኒነት እና መረጋጋት መጠበቃቸውን ያረጋግጣል።

Generic selectors
Exact matches only
Search in title
Search in content
Post Type Selectors

Public Announcement

This public notice is directed at publicly held companies established or raising capital through public subscription under the Commercial Code of Ethiopia. Specifically, it concerns companies with more than fifty (50) shareholders, regardless of the sector or industry in which they operate.
Please select either button for further information.

Capital Market Summit 2024

Be part of a groundbreaking event where industry leaders and experts will gather to explore the future of capital markets. Don’t miss your chance to connect, learn, and engage with key players in the industry. Reserve your spot now!