እንኳን ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፈቃድ ራስን የመገምገሚያ ቅጽ በደህና መጡ፡፡ ይህ ቅጽ የወደፊት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ከካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፈቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር መመሪያ ጋር በተገናኘ መልኩ ያላቸውን አቋም እንዲገመግሙ ያስችላቸዋል፡፡ ምንም አይነት ችግር ካጋጠመዎት እባክዎን እርዳታ ለማግኘት እኛን በ licensing@ecma.gov.et ላይ ለማነጋገር አያመንቱ ወይም በ 011-5-57-83-11 ይደውሉ። መመሪያዎች: አመልካቾች ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ፈቃድ ("የአገልግሎት ፈቃድ'") ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት ይህንን የራስ መገምገሚያ ቅጽ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እራስን መገምገሚያ ቅጹ እጩ አመልካቾች ለአገልግሎት ፈቃዱ ያላቸውን ዝግጁነት ደረጃ፣ እንዲሁም ጥንቃቄን፣ አስተዳደርን እና ለእያንዳንዱ የሚመለከታቸው የአገልግሎት ፈቃድ የተቀመጡ መስፈርቶች መከበራቸውን ለመገምገም የሚያስችል መመሪያ ነው፡፡ በተጠናቀቀ ራስን መገምገሚያ ቅጽ ላይ የተሰጠ አወንታዊ ምላሽ ወይም ውጤት አመልካቹ የአገልግሎት ፈቃድ እንደሚሰጠው ዋስትና አይሰጥም፡፡ አመልካቾችን የሚመለከቱ ሁሉም የራስ መገምገሚያ ቅጹ ክፍሎች መሞላት አለባቸው፡፡ምላሾችን በተገቢው ሳጥን ውስጥ ይሙሉ፤ እና አስፈላጊ ከሆነ የ√ ምልክት ያድርጉ፡፡ (*) ምልክት ማለት ለግለሰብ አመልካቾች ተፈጻሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡ (ተ/አ) ማለት ተፈጻሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡ ክፍል 1: አጠቃላይ መረጃ I. በኢትዮጵያ በሚመለከተው የመንግስት አካል የተሰጠ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ወይም የኢንቨስትመንት ፈቃድ አለዎት? አዎ አይ አመልካቹ በኢትዮጵያ በሚመለከተው የመንግስት አካል የተሰጠ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ወይም የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሊኖረው ይገባል፡፡ II. የተመዘገበ/የንግድ አድራሻ አለዎት? አዎ አይ አመልካቹ የተመዘገበ/የንግድ አድራሻ ሊኖረው ይገባል። ክፍል 2: የማህበሩ አይነት የእርስዎን የማህበር አይነት ይምረጡ፡- ምንም አልመረጡም የአክሲዮን ማኅበር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የኀብረት ሽርክና ማኅበር ሁለት ዓይነት ኃላፊነት ያለበት የሽርክና ማኀበር ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ግለሰብ/ግለሰብ ነጋዴ ክፍል 3: የጥንቃቄ መስፈርቶች ክፍል 3.1፡ የወደፊት የአገልግሎት ፈቃድ/ፈቃዶች እና የካፒታል መጠን የአገልግሎት ፈቃድ፡- እባክዎን ለማመልከት የሚፈልጉትን የአገልግሎት ፍቃድ ይምረጡ፡ (ከአንድ በላይ የአገልግሎት ፈቃዶችን ለመምረጥ የ CTRL ቁልፍን ተጭነው ይምረጡ....) ከአንድ በላይ የአገልግሎት ፈቃድ ለመምረጥ የCTRL ቁልፍን መጠቀም ይችላሉ የተመረጡ የአገልግሎት ፍቃዶች፡- ለተመረጡት ፈቃዶች የሚያስፈልግ ጠቅላላ የተጣራ ሃብት ፡ 0 የገበያ ከፋዩ የሚወሰነው በኢትዮጵያ የዋስትናዎች ገበያ ነው። 3.2፡ የሃብት ውህደት ንጽጽር # መለያ ብር '000,000 1. ገንዘብ-አከል ንብረት (ሀ) - 1.1 ጥሬ ገንዘብ 1.2 የባንክ ተቀማጭ ገንዘብ 1.3 የግምጃ ቤት ሰነዶች 1.4 የተመዘገቡ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች 1.5 ሌሎች ገንዘብ-አከል ንብረቶች 1.5.1 (እባክዎ ይግለጹ) ጠቅላላ ገንዘብ-አከል ንብረቶች 0 2. ጠቅላላ ንብረቶች (ለ) ገንዘብ-አከል ንብረቶች ከጠቅላላ ንብረቶች ያላቸው ንጽጽር 0 ክፍል 4፡ አስተዳደራዊ መስፈርቶች 4.1 አስተዳደራዊ መዋቅር አስተዳደራዊ መዋቅር፡- 4.1.1. አመልካቹ የዳይሬክተሮች ቦርድ አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ ቢያንስ ሶስት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊኖረው ይገባል። 4.1.2. ዳይሬክተሮች በካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፈቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር መመሪያ የብቃት ማዕቀፍ ውስጥ የተገለጹትን መመዘኛዎች ያሟላሉ ወይ ? አዎ አይ ተ/አ ዳይሬክተሮች በካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፈቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር መመሪያ የብቃት ማዕቀፍ ውስጥ የተገለጹትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡ 4.1.3. የቦርድ ቻርተር አለ? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የቦርድ ቻርተር ሊኖረው ይገባል። 4.1.4. የሰብሳቢው እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር/ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦታ የተለየ ነው? አዎ አይ ተ/አ የሰብሳቢው እና የማኔጂንግ ዳይሬክተር/ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦታ የተለየ መሆን አለበት፡፡ 4.1.5. ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ/ዋና ስራ አስፈፃሚው በካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፈቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር መመሪያ ውስጥ የተገለጹትን መስፈርቶች ያሟላሉ ወይ ? አዎ አይ ተ/አ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ/ዋና ስራ አስፈፃሚው በካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፈቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር መመሪያ ውስጥ የተገለጹትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡ 4.1.6. የአመልካች ቦርድ የሚከተሉት ንዑስ ኮሚቴዎች አሉት? 4.1.6ሀ. ሿሚ እና አስመራጭ ኮሚቴ? አዎ አይ ተ/አ የአመልካቹ ቦርድ የሿሚ እና አስመራጭ ንዑስ-ኮሚቴ ሊኖረው ይገባል። 4.1.6ለ. የአደጋ ስጋት አስተዳደር እና ተገዥነትን የሚያረጋግጥ ኮሚቴ? አዎ አይ ተ/አ የአመልካቹ ቦርድ የአደጋ ስጋት አስተዳደር እና የተገዥነት ንዑስ-ኮሚቴ ሊኖረው ይገባል። 4.1.6ሐ. የኦዲት ኮሚቴ? አዎ አይ ተ/አ የአመልካቹ ቦርድ የኦዲት ንዑስ-ኮሚቴ ሊኖረው ይገባል። 4.1.7. አመልካቹ የኩባንያው ፀሐፊ ወይም አቻ አካል አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የኩባንያ ፀሐፊ ወይም አቻ አካል ሊኖረው ይገባል። ክፍል 5: ሌሎች የአሠራር መስፈርቶች 5.1 የአሠራር ዝግጁነት 5.1.1. የመሠረተ ልማት ዝግጁነት፡- 5.1.1ሀ. የአመልካቹ የንግድ ቦታ ለስራ ዝግጁ ነው? አዎ አይ ተ/አ የአመልካቹ የንግድ ቦታ ለስራ ዝግጁ መሆን አለበት። 5.1.1ለ. የአይቲ ሃርድዌር ውቅሮች እና የሶፍትዌር መተግበሪያዎች አሉ? አዎ አይ ተ/አ ለስራ የሚያገለግሉ የአይቲ ሃርድዌር ውቅሮች እና የሶፍትዌር መተግበሪያዎች ሊኖሩ ይገባል። 5.1.1ሐ. ስልኮች እና የድምጽ መቅጃ መሳሪያዎች አሉት? አዎ አይ ተ/አ ስልኮች እና የድምጽ መቅጃ መሳሪያዎች ሊኖሩ ይገባል። 5.1.2. የመዝገብ አያያዝ 5.1.2ሀ. አመልካቹ መረጃን ለማከማቸት እና ለማውጣት ተገቢ አሰራሮች እና ሂደቶች አሉት? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ መረጃን ለማከማቸት እና ለማውጣት ተገቢ ስርዓቶች እና ሂደቶች ሊኖሩት ይገባል። 5.1.2ለ. አመልካቹ የውስጥ ሰነድ የማቆየት ፖሊሲ አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የውስጥ ሰነድ የማቆየት ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል። 5.1.3. የአሠራር ሂደቶች እና መስፈርቶች 5.1.3ሀ. አመልካቹ ዝርዝር የአሠራር መመሪያ አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ ዝርዝር የአሠራር መመሪያ ሊኖረው ይገባል። 5.1.3ለ. አመልካቹ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግብይት ፖሊሲ አለው?* አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግብይት ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል። 5.1.3ሐ. አመልካቹ የራሱን ካፒታል ተጠቅሞ ግብይቶችን የሚያካሂድበት የንግድ ፖሊሲ አለው?* አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የራሱን ካፒታል ተጠቅሞ ግብይቶችን የሚያካሂድበት የንግድ ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል። 5.1.3መ. አመልካቹ ለሰራተኞች የምግባር/የሥነ ምግባር ደንብ አለው?* አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ ለሰራተኞች የምግባር/የሥነ ምግባር ደንብ ሊኖረው ይገባል። 5.1.3ሠ. አመልካቹ የጥቅም ግጭት ፖሊሲ አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የጥቅም ግጭት ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል። 5.1.3ረ. አመልካቹ የተገዥነት መመሪያ አለው?* አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የተገዥነት መመሪያ ሊኖረው ይገባል። 5.1.3ሰ. አመልካቹ በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን መከላከልን የሚመለከት መመሪያ አለው?* አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የ AML/CFT መመሪያ ሊኖረው ይገባል። 5.1.3ሸ. አመልካቹ የግጭት መፍቻ ማዕቀፍ አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የግጭት መፍቻ ማዕቀፍ ሊኖረው ይገባል። 5.1.3ቀ. አመልካቹ የታወቀ ራሱን በራሱ የሚቆጣጠር ድርጅት ወይም የኢንዱስትሪ ማህበር አባል ነው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የታወቀ የSRO ወይም የኢንዱስትሪ ማህበር አባል መሆን አለበት። 5.1.3በ. አመልካቹ መደበኛ የደንበኛህን እወቅ ማእቀፍ አሰራር አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ መደበኛ የ KYC አሰራር ሊኖረው ይገባል። 5.1.3ተ. አመልካቹ የታማኝነት መድን ዋስትና አለው፤ ወይ የማግኘት ሂደቱን ጀምሯል? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የታማኝነት ዋስትና ሊኖረው ወይም የማግኘት ሂደቱን መጀመር አለበት። 5.1.3ቸ. አመልካቹ ስልታዊ የንግድ እቅድ አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ ስልታዊ የንግድ እቅድ ሊኖረው ይገባል። 5.1.3ነ. አመልካቹ ኦዲት የተደረገ የአንድ አመት የፋይናንስ መግለጫ ወይም የድርጊቶች መግለጫ ወይም የሶስት (3) ወራት የስራ አመራር ሂሳብ አለው?* አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የሙሉ አመት ኦዲት የተደረገ የፋይናንስ መግለጫ ወይም የድርጊቶች መግለጫ ወይም የሶስት (3) ወራት የአመራር ሂሳብ ሊኖረው ይገባል። 5.2 የቴክኖሎጂ መስፈርቶች 5.2.4. ስርዓቶች እና ቁጥጥር :- 5.2.4ሀ. አመልካቹ የአደጋ ስጋት አስተዳደር እና ተገዥነትን የሚያረጋግጡ እና የደህንነት ህግ ጥሰቶችን ለመከላከል፣ ለመለየት እና ለማስተካከል ያለሙ ሂደቶች እና አጥጋቢ ስርዓቶች አሉት? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ስርዓቶች እና የደህንነት ህግ ጥሰቶችን ለመከላከል፣ ለመለየት እና ለማረም የታለሙ የተገዥነት ስርዓቶች እና ሂደቶች ሊኖሩት ይገባል። 5.2.4ለ. አመልካቹ ከአደጋ የማገገሚያ እና የንግድ ሥራ ቀጣይነት ሂደት አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ ከአደጋ የማገገሚያ እና የንግድ ቀጣይነት ሂደት ሊኖረው ይገባል። 5.2.4ሐ. አመልካቹ የዳታ ግላዊነት ፖሊሲ አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የዳታ ግላዊነት ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል። 5.2.4መ. አመልካቹ የሳይበር ጥቃት አደጋዎችን ለመቋቋም የተዘጋጁ ሂደቶች አሉት? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የሳይበር አደጋዎችን ለመቋቋም የሚያስችሉ ሂደቶች ሊኖሩት ይገባል። 5.3 የሰው ሃብት መስፈርቶች 5.3.5. ሰራተኞች፡- 5.3.5ሀ. አመልካቹ ለአገልግሎት ፈቃዱ/ፈቃዶች ተሿሚ እንደራሴ በመሆን የሚሾሙትን ግለሰቦች ለይቷል? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ ለአገልግሎት ፈቃድ(ዎች) የተሿሚ ተወካይ ሆነው የሚሾሙ ግለሰቦችን መለየት አለበት። 5.3.5ለ. አመልካቹ የተገዢነት ኦፊሰር አለው? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ የተገዢነት ኦፊሰር ሊኖረው ይገባል። 5.3.5ሐ. አመልካች ድርጅቱን ለማስተዳደር በቁጥር፣ በብቃትና ልምድ በቂ ሰራተኞች አሉት? አዎ አይ ተ/አ አመልካቹ ኩባንያውን ለማስኬድ በቁጥር፣ በብቃት እና በልምድ በቂ ሰራተኞች ሊኖሩት ይገባል። በራስ-ግምገማ ሂደት ውስጥ ስለተሳተፉ እናመሰግናለን። ሆኖም፣ የሰጡት ምላሽ ከካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች የፈቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር መመሪያ ጋር ሙሉ በሙሉ እንደማይጣጣም ልናሳውቅዎ እንወዳለን። ለእርስዎ ግምገማ ፒዲኤፍ ተዘጋጅቶ ወርዷል። ቢሆንም፣ አሁንም ለፈቃዱ ማመልከት ከፈለጉ፣ ቅጾቹን ለማግኘት ከታች ያለውን ቁልፍ መጫን ይችላሉ። ለማንኛውም ቅጾቹን አውጣ