ኢንቬስተሮችን ከማጭበርበር/ ከመጭበርበር ለመጠበቅ እና ፍትሐዊ አያያዝን/ አገልግሎትን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነን። ፈቃድ ካላቸው አገልግሎት አቅራቢዎች እና ከተመዘገቡ ተቋማት ጋር ብቻ ይሥሩ። በመረጃ የተደገፈ የመዋዕለ ንዋይ/ የኢንቨሰትመንት ውሳኔ ለማድረግ የአደጋ መገለጫዎን/ ተጋላጭነት ደረጃዎን ይረዱ። እርዳታ ለማግኘት ፈቃድ ካለው ባለሙያ ምክር ይጠይቁ፣ እንዲሁም መረጃዎቻችንን ይከታተሉ።
አንዱ ተቀዳሚ ዓላማችን ኢንቨስተሮችን ከመጭበርበር እና ከሕገ ወጥ ተግባራት መጠበቅ ነው። ኢንቨስተሮች ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዲስተናገዱ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን። ይህንንም ለማሳካት በኢንቨስተሮች እና በማንኛውም ፈቃድ በተሰጣቸው አካላት መካከል በሚደረጉ የንግድ ልውውጦች የሚነሱ ቅሬታዎችን በማስተናገድ ስልታዊ አሠራርን እንከተላለን። የካፒታል ገበያዎችን ውስብስብነቶች በራስ መተማመን እና ደህንነትን እንዲያልፉ ለማገዝ ቆርጠን ተነስተናል።
ሁሉም ኢንቨስትመንቶች የተለያዩ አደጋዎችን/ የአደጋ ስጋቶችን ይይዛሉ። በገበያ ላይ ያሉትን የተለያዩ የፋይናንሺያል/የፋይናንስ ኢንቬስትመንት ምርቶችን መረዳት፣ እያንዳንዳቸውን መተንተን እና በመረጃ ላይ የተመሠረተ ምርጫ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ከመገለጫዎ ጋር የሚስማማ ተጋፋጭ፣ መጠነኛ ወይም ቁጥብ የኢንቨስትመንት ስትራቴጂ ለመከተል “የአደጋ ስጋትን የሚወስድ” ወይም “የአደጋ ስጋትን የሚጠላ/ የሚያስዎግድ” ግለሰብ መሆንዎን ይወስኑ።
የእርስዎን የአደጋ ስጋት የመቋቋም አቅም በመረዳት እና የመዋዕለ ንዋይ/የኢንቨስትመንት አማራጮችዎን በጥልቀት በመመርመር የበለጠ በመረጃ የተደገፈ ውሳኔዎችን ማድረግ እና የፋይናንስ ግቦችዎን የማሳካት እድልዎን ከፍ ማድረግ ይችላሉ። ያስታውሱ፣ በሚጠራጠሩበት ጊዜ የባለሙያ ምክር መፈለግ በጣም ጠቃሚ/አስፈላጊ ነው።
ትክክለኛውን የኢንቨስትመንት ምርጫ ለማድረግ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ ፈቃድ ካለው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ባለሞያ አቅራቢ ምክር ይጠይቁ። እነዚህ ባለሙያዎች የእርስዎን ስጋት መገለጫ ለመረዳት፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመተንተን እና የተበጀ የኢንቨስትመንት ስትራቴጂ ለመፍጠር ያግዙዎታል።