የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ልማት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እና የ10-አመት ልማት እቅድ ቁልፍ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች ዋነኛው ሲሆን በካፒታል ገበያ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1248/2013 ዓ.ም) ስር የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ተቋቁሟል። ሆኖም እንደ ውስን የምክር አገልግሎት፣ የቁጥጥር ማዕቀፍ ዕውቀት ክፍተቶች እና ዝቅተኛ የገበያ ተሳትፎ ያሉ ተግዳሮቶች የገበያው እድገት ላይ ተጽእኖ አሳድረዋል። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የኢ.ካ.ገ.ባ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የመጀመሪያ ዙር የሕዝብ ሽያጭ ክሊኒክ በመክፈት ለሕዝብ ገበያ ለሚዘጋጁ ኩባንያዎች የቴክኒክ መመሪያና ድጋፍ በመስጠት የሽያጭ ዝግጁነት እንዲገመግሙና መዋቅራዊ ፈተናዎችን እንዲያሸንፉ በማድረግ እና የገበያ ተሳትፎን በማጎልበት የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ዕድገት በማፋጠን ላይ ይገኛል።
ይህ ክሊኒክ በኢ.ካ.ገ.ባ ስር የፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ሆኖ ተቋቁሞ አክሲዮኖችን በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በማውጣት ወይም በመመዝገብ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ የሆኑ ኩባንያዎችን እንዲያቀርብ ሀላፊነት ተሰጥቶታል። ክሊኒኩ የሚንቀሳቀሰው ከኢ.ካ.ገ.ባ ቁጥጥር እና ሌሎች ድርጊቶች ነጻ በመሆን ሲሆን ከኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ጋር አነስተኛ ግንኙነት ይኖረዋል።
የመጀመሪያ ዙር የሕዝብ ሽያጭ ክሊኒክ የተዋቀረ የድጋፍ መርሃ ግብር በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ይሰራል፤ በዚህም በክሊኒኩ ውስጥ የገቡ ኩባንያዎች ለመጀመሪያ ዙር የሕዝብ ሽያጭ ዝግጁነት ያላቸውን ክፍተቶች ለመለየት የዝግጁነት ግምገማዎችን ያካሂዳሉ ፣የተለዩትን ክፍተቶች ለማስተካከል የቴክኒክ መመሪያ እና ድጋፍ ያገኛሉ ፣በአቅም ግንባታ እና የስልጠና ፕሮግራሞች ላይ ይሳተፋሉ እና ሽያጩ ዝግጅት ይጀምራሉ።
ክሊኒኩ የተመረጡ ኩባንያዎችን ወደ ህዝብ ለማቅረብ በሚያስፈልጉት መስፈርቶች እና ሂደቶች ላይ በማስተማር የካፒታል ገበያዎችን ለዕድገትና ለመስፋፋት እንዲጠቀሙ በማድረግ ላይ ያተኩራል።
የክሊኒኩ ዋና ተልእኮዎች የሚከተሉት ናቸው፦
ክሊኒኩን ለመቀላቀል ድርጅቶች፦
The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) as per Articles 86(4), 87(1) and (2), 90(3) and 108 of the Capital Market Proclamation No. 1248/2021, has prepared a draft directive on Collective Investment Schemes (CIS). The draft directive provides a framework for the registration, operation, and supervision of collective investment schemes. To acces the draft directive please click the buttons below.
Be part of a groundbreaking event where industry leaders and experts will gather to explore the future of capital markets. Don’t miss your chance to connect, learn, and engage with key players in the industry. Reserve your spot now!