
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር ሀና ተኸልቁ በቻይና ሶስት ከተሞች ሻንጋይ፣ ሃርቢን እና ቾንግኪን በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ በፋይናንሱ ዘርፍ በተለይም በካፒታል ገበያው ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን እና ሀገራችን ለቻይና ባለሀብቶች ያላትን ምቹ ሁኔታ እና ትልቅ አቅም አስተዋውቀዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ በቻይና ቆይታቸው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውጤታማ ውይይት ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አቅምን ለማሳደግ በትብብር ሊሰሩ በሚችሉ ስራዎች ዙሪያ በቻይና ከሚገኘው ከሃርቢን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች ጋርም በሰፊው መክረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሀርቢን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አለም አቀፍ የዶክትሬት መርሃ ግብር የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ይሄም ኢትዮጵያ እና ቻይና በትምህርት እና ፋይናንስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እድል የፈጠረ ነው፡፡
በአጠቃላይ የነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ በፋይናንሱ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም በቻይና ለሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ማስተዋወቅ የቻለችበት ብሎም ከቻይና ጋር ያላትን ዘመን የተሻገር ግንኙነት ያጠናከረችበት ነበር፡፡
