
ባለስልጣኑ በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ የሚገኘውን 18ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን ከሰራተኞች ጋር በመሆን የብሄራዊ መዝሙር በመዘመር እና በዓሉን በሚመለከት የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ ላይ ውይይት በማድረግ አክብሯል፡፡
በውይይቱ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ክብር በአባቶቻቸን የተከፈለው ዋጋ ትልቅ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ቀጣይነት ባለው መልኩ የአሁኑ ትውልድም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ክብር ጠብቆ ማቆየት እንዲችል መስራት እንደሚገባም በውይይቱ ተነስቷል፡፡
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሀገራችን የኩራት መገለጫ የሆነው ሰንደቅ አላማችን የሚከበርበትን 18ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን በስኬት በማክበሩ ደስታ ይሰማዋል፡፡
