ECMA / ኢካገባ

ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ የማስማማት እና የግልግል ዳኝነት ማዕከል በጋራ በሚሰራቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ  ውይይት አደረገ፡፡

WhatsApp Image 2025 07 23 at 14.15.29 5f62cc89

አዲስ አበባ

ሀምሌ 17/2017 የኢካገባ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገብያ ባለስልጣን  እና የኢትዮጵያ የማስማማት እና የግልግል ዳኝነት ማዕከል በጋራ በሚሩባቸው የትብብር ማዕቀፍ ዙሪያ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ የካፒታል ገብያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልኩን ጨምሮ የኢትዮጵያ የማስማማት እና የግልግል ዳኝነት ማዕከል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ECMA and Ethiopian Mediation and Arbitration Center EMAC discuss to Forge Partnerships to Strengthen Capital Market Dispute Resolution 2

በጋራ ውይይቱ አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎችን በተመለከተ እንዲሁም አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች በካፒታል ገበያ ውስጥ ስላላቸው ከፍተኛ ሚና ውይይት ተደርጓል ፡፡

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በካፒታል ገበያው ውስጥ የሚኖሩ ግጭቶች በሽምግልና፣ በግልግል ዳኝነት እንዲፈቱ ስለግልግል ዳኝነት አሰራር እና ከግልግል ዳኝነት ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በተመለከተ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 የተሰጡትን ተግባራት ለመከወን የረዥም ግዜ ልምድ ካለው ከኢትዮጵያ የማስማማት እና የግልግል ዳኝነት ማዕከል ጋር በቅንጅት ለመስራት ያለውን ተነሳሽነትም ገልጿል፡፡