በሱፈቃድ ተረፈ ባለፈው ጽሑፍ ስለካፒታል ገበያ ምንነት፣ ፋይዳና ታሪካዊ ዳራ በመጠኑ ለመግለጽ ሞክሬያለሁ። በማስከተል ስለካፒታል ገበያ ተዋናዮች እንደምጽፍ ጠቁሜ የነበረ ቢሆንም፣ ቅድሚያ ሰጥቼ አንባቢያን ማወቅ አለባቸው ያልኩትን ጉዳይ አብራራለሁ፡፡ በዚህ ጽሑፍ የካፒታል ገበያ የቁጥጥር መሣሪያዎች ከሆኑት አንዱና ዋነኛ ስለሆነው የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች፣ ማለትም በተለምዶ የአክሲዮንና የቦንድ ሰነዶች የሚባሉትን በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ማስመዝገብ ስለሚኖረው ፋይዳ፣ አውጪዎች […]