እንዴት ማመልከት ይቻላል

እንዴት ማመልከት ይቻላል

አዲስ ነገር ለመፍጠር ዝግጁ ነዎት? ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ሴክተር በሚገባ የተቀረጸ አዲስ መፍትሔ አለዎት? የቁጥጥር ሳንድቦክስ የመጀመሪያ ዙር ተሳታፊነት ማመልከቻዎች ለ30 ቀናት ክፍት ሲሆኑ በመስከረም 20፣ 2017 ይዘጋሉ። የማመልከቻውን ሂደት እና የብቁነት መስፈርት በዚህ ድህረ ገጽ ላይ መዳሰስ/ማግኘት እና መመልከት ይችላሉ።

የማመልከቻ ሂደት

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የቁጥጥር ሳንድቦክስ ፕሮግራም ማመልከቻ በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል። ሁሉንም ጥያቄዎች በደንብ መመለስዎን በማረጋገጥ የማመልከቻ ቅጹን በጥንቃቄ ይገምግሙ እና ይሙሉ።

የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ያስታውሱ:-

ማሳሰቢያ፡- በECMA የቁጥጥር ሥልጣን ስር የካፒታል ገበያ አገልግሎት ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ያላቸው ድርጅቶች የሚከተሉትን ልዩ ቅድመ ሁኔታዎች ካሟሉ ወደ ሳንድቦክሱ ለመግባት ከግምት ውስጥ ይገባሉ።

  1. በኢትዮጵያውያን ሸማቾች ላይ ማተኮር፡- የቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ በዋናነት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሸማቾች ላይ ማተኮር እና እነርሱን ተጠቃሚ ማድረግ አለበት።
  2. እውነተኛ ፈጠራ፡- መፍትሄው በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች የተለየ አዲስ ነገር ማቅረብ አለበት። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂን፣ የመላኪያ ቻናሎችን ወይም የንግድ ሞዴሎችን ሊያካትት ይችላል።
  3. የሸማቾች ተጠቃሚነት፡- መፍትሄው ለኢትዮጵያውያን ሸማቾች ግልጽ የሆኑ ጥቅሞችን የሚሰጥ እና በተለይም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን እና ጀማሪዎችን በመደገፍ ላይ የሚያተኩር መሆን አለበት።
  4. ለሙከራ ዝግጁ:- የአመልካቹ ድርጅት በቀጥታ ገበያ ውስጥ እውነተኛ ደንበኞች ላይ መፍትሄዎቻቸውን ለመሞከር ዝግጁ መሆን አለባቸው። ይህም ሁሉንም አስፈላጊ አጋርነት እና የሸማቾች ጥበቃ እርምጃዎችን የያዘ ሙሉ በሙሉ የሚሰራ ምርትን ወይም አገልግሎትን መያዝን ያስገድዳል።
  5. የቁጥጥር ድጋፍ አስፈላጊነት፡- ማመልከቻው ሳንድቦክሱ የሙከራ ሂደቱን እንዴት እንደሚረዳ በግልፅ ማብራራት አለበት። ይህ የቁጥጥር ማብራሪያ መፈለግን፣ አሻሚዎችን ጉዳዮችን መሻገርን፣ ቁጥጥር በተደረገበት አካባቢ መሞከርን ወይም ለቀጣይ እድገት ግብረ መልስ መቀበልን ሊያካትት ይችላል።

የማመልከቻ ቅጽ

በቁጥጥር ሳንድቦክስ ላይ ስላለዎት ፍላጎት እናመሰግናለን። የዚህ ዙር ማመልከቻ ማስገቢያ ጊዜ አሁን አልፏል። እባክዎ ስለሚቀጥለው ዙር እና የወደፊት የተሳትፎ እድሎች መረጃ ለማግኘት በቅርቡ ተመልሰው ይመልከቱ።

ቀጣይ እርምጃዎች

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሁሉንም ማመልከቻዎች ይመረምራል። የማመልከቻ መስኮቱ ካለቀ በኋላ በሦስት ሳምንታት ውስጥ ውጤቱን ለአመልካቾች እናሳውቃለን።
ለሳንድቦክሱ ከተመረጡ፣ ስለ የእርስዎ የሙከራ እቅድ ለመወያየት እና ማንኛውንም አስፈላጊ የቁጥጥር መሣሪያዎችን ለማቅረብ እንገናኛለን። የሳንድቦክሱ ሂደት የሚከተሉትን ያካትታል:-

  • የሙከራ ዕቅድ ስምምነት፡ ለፈጠራዎ ግልጽ የሆነ የሙከራ ዕቅድን ለመቅረጽ ከእኛ ጋር ይተባበራሉ/አብረው ይስሩ።
  • የቁጥጥር መሳሪያዎች፡- ለሳንድቦክሱ አካባቢ የተወሰኑ አስፈላጊ የቁጥጥር መሳሪያዎችን ወይም ነፃነቶችን ይቀበላሉ።
  • የሙከራ ወቅት፡- ቁጥጥር በሚደረግበት አካባቢ ከእውነተኛ ደንበኞች ጋር ሙከራዎን ያካሂዳሉ።
  • የመውጫ ስትራቴጂ፡- በተሳካ ሙከራ መፍትሄዎን ወደ ሰፊው ገበያ ለማሸጋገር እቅድ ያውጡ።

ያግኙን!

ስለ ኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የቁጥጥር ሳንድቦክስ ጥያቄዎች አሉዎት? እኛ ለመርዳት እዚህ ነን! በ regulatorysandbox@ecma.gov.et ላይ እኛን ያግኙን፣ የቡድናችን አባል እርስዎን በደስታ ይረዱዎታል።

Generic selectors
Exact matches only
Search in title
Search in content
Post Type Selectors

Public Announcement

This public notice is directed at publicly held companies established or raising capital through public subscription under the Commercial Code of Ethiopia. Specifically, it concerns companies with more than fifty (50) shareholders, regardless of the sector or industry in which they operate.
Please select either button for further information.

Capital Market Summit 2024

Be part of a groundbreaking event where industry leaders and experts will gather to explore the future of capital markets. Don’t miss your chance to connect, learn, and engage with key players in the industry. Reserve your spot now!