የቁጥጥር ሳንድቦክስ

ይፍጠሩ ፣ ይሞክሩ ፣ ይለውጡ

ወደ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ፈጠራ መግቢያ በር እንኳን በደህና መጡ። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ኢ.ካ.ገ.ባ) ፈር ቀዳጅ ፕሮግራም የሆነው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ቁጥጥር ሳንድቦክስ ከኢኖቬቲቭ ፋይናንሺያል ላብ (አይ.ኤፍ.ኤል) ጋር በመተባበር ለታዳጊ እና ለተቋቋሙ ድርጅቶች አዲስ የካፒታል ገበያ ምርቶችን፣ አገልግሎቶችን እና የንግድ ሞዴሎችን እንዲሞክሩ ተለዋዋጭ/ዘርፈ ብዙ መድረክ ይሰጣል።

የቁጥጥር ሳንድቦክሱን መጠቀም ለምን ያስፈልጋል?

የቁጥጥር መመሪያ

በECMA ቀጥታ ድጋፍ የካፒታል ገበያ ደንቦችን ውስብስብነቶች መሻገር ይችላሉ

ደኅንነቱ የተጠበቀ የሙከራ አካባቢ

ፈጠራዎችዎን ሙሉ በሙሉ በገበያ ማሰማራት የሚያመጣው ጫና ሳይኖር ፈጠራዎችዎን ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ይሞክሩ።

ፈጥኖ ወደ ገበያ መግባት

ለእርስዎ የተበጀ ምክር በማግኘት እና ቢሮክራሲያዊ መሰናክሎችን በመቀነስ ከፅንሰ-ሀሳብ ተነስተው ወደ ገበያ የሚደርሱበትን ፍጥነት ይጨምሩ።