ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ይህ ገዕ ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ይዳስሳል።

የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 እና የሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ (መመሪያ ቁጥር: 1030/2017) ስለ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ምዝገባ አስመልክቶ ስላስቀመጡት ግዴታዎች ጠቅለል ያለ ጥያቄ እና መልስ

የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 እና የሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ (መመሪያ ቁጥር: 1030/2017) ሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጪዎች ላይ ምን ግዴታዎችን አስቀምጠዋል (ጥሎአል)?

በጥቅሉ አዋጁ እና መመርያው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ  አውጪዎች ላይ ሁለት ግዴታዎችን አስቀምጠዋል፤

ሀ. ሰነደ ሙዓለ ንዋዮቻቸውን ያወጡ፣ በማውጣት ሂደት ላይ ያሉ ወይም ሰነደ ሙዓለ ንዋዮቻቸውን ለህዝብ ለማውጣት የሚፈልጉ ኩባንያዎች ሰነደ ሙዓለ ንዋዮቻቸውን በባለስልጣኑ እንዲያስመዘግቡ፤ (የአዋጁ አንቀጽ 75(1) እና የመመሪያው አንቀጽ 4)፤ እና

ለ. በሕዝብ ባለቤትነት የተያዘ ኩባንያ ወይም በሕዝብ ባለቤትነት የተያዙ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች አውጪ ለባለስልጣኑ ቀጣይነት ያለው ሪፖርት የማቅረብ (የአዋጁ አንቀጽ (1) እና የመመሪያው አንቀጽ 135 (1))፤

ግዴታን አስቀምጧል።  

የሰነደ ሙአለ ንዋዮች ምዝገባ እና በቋሚነት ሪፖርት የማቅረብ ግዴታዎች አላማቸው ኢንቬስተሮች በመረጃ ላይ የተመረኮዘ የኢንቨስትመንት ውሳኔ መወሰን ይችሉ ዘንድ ስለሰነደ ሙአለ ንዋይ አውጪው፣ ስለንግዱ፣ ስለፋይናንስ ሁኔታው፣ ስለሽያጩ እና ሊኖሩ ስለሚችሉ ተያያዥ ስጋቶች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በቂ እና ትክክለኛ በሆነ ሁኔታ ይፋ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው።

አዎ።  ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን የማስመዝገብ ግዴታ በማንኛው አይነት የስራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎ ላይ የተጣለ ግዴታ ነው፡፡

ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን የማስመዝገብ ግዴታ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 አንቀጽ 75 (1) ላይ የተደነገገ ሲሆን የምዝገባው ዝርዝር መስፈርቶች ደግሞ ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2017 ላይ በዝርዝር ተገልጸዋል። በዚህም መሰረት ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለማስመዝገብ የሚቀርብ የምዝገባ መግለጫ ሊያካትታቸው የሚገቡ ነግሮች በመመሪያው አንቀጽ 8 ላይ የተገለጹ ሲሆን እነዚህም በጥቅሉ የሚከተሉት ናቸው፦

ሀ/ ስልጣን ባለው ሀላፊ ወይም የግብይት አማካሪ የተፈረመ ደብዳቤ፤

ለ/ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ (የደንበኛ ሳቢ መግለጫ ይዘቶች በመመሪያው ከአንቀጽ 77 እስከ 134 ድረስ ተደንግገው ይገኛሉ)፤ እንዲሁም፣

ሐ/ ደጋፊ መረጃዎች እና ሰነዶች (በመመሪያው አንቀጽ 8 (1) (ሐ) ላይ ተደንግገው የሚገኙ) ናቸው።

መመሪያው ማንኛውም ለህዝብ የሚቀርብ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ በባለስልጣኑ እንዲመዘገቡ ያስገድዳል። ይሁን እንጂ የምዝገባ ሂደቱ እና የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳው እንደ አቅርቦቱ የግዜ ሰሌዳ መሰረት ይለያያል። በዚህ መሰረት በመመርያው የመሸጋገርያ ድንጋጌ (አንቀጽ 159) ሥር የተጠቀሱ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ምዝገባ ከዚህ በታች ነጥብ (ሀ) እና (ለ) ላይ በተገለጸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መከናወን አለበት። በዚህ አንቀጽ 159 ውስጥ ያልተካተቱ ሌሎች የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አቅርቦቶች ደግሞ ከዚህ በታች  በነጥብ (ሐ) ላይ በተገለጸው መሰረት መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ሀ. መመሪያው ከመውጣቱ በፊት የተደረጉ የህዝብ ሽያጭ አቅርቦቶች እና የሽያጭ ሂደታቸው የተጠናቀቀ አቅርቦቶችን በሚመለከት ሰነደ ሙዓለ ነዋዮቹ መመሪያው በወጣ በ12 ወራት ውስጥ መመዝገብ አለባቸው።

ለ. መመሪያው ከመውጣቱ በፊት የህዝብ ሽያጭ አቅርቦታቸው የተጀመረ እና መመሪያው ከወጣ በኋላም ቢሆን የሽያጭ ሂደታቸው ያልተጠናቀቀ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ አቅርቦቶችን በሚመለከት የቀረቡትን ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች መመሪያው በወጣ በ12 ወራት ውስጥ ማስመዝገብ አለባቸው፤ እና

ሐ. ማንኛውም ከመመሪያው መውጣት በኋላ የሚደረጉ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ አቅርቦቶች በሚመለከት በመመሪያው ላይ በተደነገገው መሰረት አቅርቦቱ ከመጀመሩ በፊት ሰነደ ሙዓለ ነዋዮቹ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።

ማናቸውም ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ለሽያጭ ለህዝብ ከመቅረባቸው በፊት በባለሥልጣኑ መመዝገብ አለባቸው፡፡

  • መመሪያው ከመውጣቱ በፊት ለህዝብ ሽያጭ መቅረብ የጀመሩ ሽያጫቸው ግን ያልተጠናቀቀ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን በተመለከተ ግን በተጀመረው ሁኔታ ሽያጫቸው እንዲቀጥሉ እና ምዝገባቸን በአንቀጽ 159(2) መመሪያው ከጸደቀ እለት ጀምሮ ባሉት 12 ወራት ጊዜ ውስጥ (ህዳር 2018 በፊት) ሰነደ ሙዓለ ንዋዮቹን ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል::
  • መመሪያው ከወጣ በኋላ የሚወጡ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ስለ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ምዝገባ በተቀመጡት የመመሪያው ድንጋጌዎች መሰረት ሰነደ ሙዓለ ንዋዮቹ ለሽያጭ ለህዝብ ከመቅረባቸው በፊት በባለሥልጣኑ መመዝገብ አለባቸው::
  • አንድ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ለሕዝብ ሽያጭ ቀረበ የሚባለው ለግዢ ቃልኪዳን የማቅረብ ግብዣ ሲከናወን ነው። ይህ ማለት፡
    1. ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ለሽያጭ የሚያቀርበው ድርጅት አዲስ የሚቋቋም ድርጅት ከሆነ ለሕዝብ ሽያጭ አቀረበ የሚባለው በንግድ ህጉ አንቀጽ 259 መሰረት አስፈላጊውን መረጃ ያካተተ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ አዘጋጅቶ በሁሉም አደራጆች ተፈርሞ የግዙኝ ጥያቄ የቀረበበት ቀን ሲሆን፤
    2. ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ለሽያጭ የሚያቀርበው ድርጅት ነባር ድርጅት ከሆነ ደግሞ ለሕዝብ ሽያጭ ቀረበ የሚባለው ድርጊቱን (ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ለሽያጭ ማቅረብን) ለመወሰን ህጋዊ ስልጣን ባለው የድርጅቱ አካል ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ድርጅቱ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮቹን ለሽያጭ የሚቅርቡበትን መንገድ፤ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ዋጋ እና መጠን፤ ግዜ፤ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን የያዘ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ አዘጋጅቶ የግዙኝ ጥያቄውን ያቀረበበት ግዜ ማለት ነው።

ስለሆነም ካፒታሉን ሰነደ ሙዓለ ንዋዮን ለህዝብ ሽያጭ በማቅረብ ለማሳደግ ለሚፈልግ ነባር ድርጅት  ሰነደ ሙዓለ ንዋዮቹን ለሽያጭ አቀረቡ የሚባለው የጠቅላላ ጉባኤው ባሳለፈው የካፒታል ማሳደግ ውሳኔ መሠረት ድርጅቱ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 455 መሰረት ሰነደ ሙዓለ ንዋዮቹን ለሽያጭ የሚያቅርብበትን ወሳኝ መረጃዎችን አካቶ የግዙኝ ጥያቄውን ያስተላልፍበት ቀን ማለት ነው።

ይህ በይፋዊ መግለጫ መሰረት የቀረበው መረጃ  በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 እና በሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለህዝብ የማቅረብ እና ግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2024 በተደነገገው መሰረት በባለስልጣኑ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ማስመዝገብ አይደለም፡፡

ስለሆነም የይፋዊ መግለጫው ዓላማ የሽግግር ድንጋጌዎቹ የሚተገበሩባቸውን እና በመደበኛ የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መከናወን ያለባቸውን የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች  ለመለየት ነው፡፡ 

ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ ያቀረበ እና በህዝብ ባለቤትነት የተያዙ ኩባንያዎች ሁሉ በቋሚነት መረጃን ይፋ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

በቋሚነት መረጃን ይፋ የማድረግ ግዴታ በቋሚነት በየግማሽ-ዓመቱ መከናወን የሚገባው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጪዎች አንዳንድ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ዋጋ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ መረጃዎችን በ24 ሰአታት ውስጥ ለባለሥልጣኑ እና ለሕዝብ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡

Generic selectors
Exact matches only
Search in title
Search in content
Post Type Selectors

Public Announcement

This public notice is directed at publicly held companies established or raising capital through public subscription under the Commercial Code of Ethiopia. Specifically, it concerns companies with more than fifty (50) shareholders, regardless of the sector or industry in which they operate.
Please select either button for further information.

Capital Market Summit 2024

Be part of a groundbreaking event where industry leaders and experts will gather to explore the future of capital markets. Don’t miss your chance to connect, learn, and engage with key players in the industry. Reserve your spot now!