የካፒታል ገበያ ቁጥጥር ማድረግ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከተቋቋመበት ዋና ተልዕኮ አንዱ ነው። በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ከፍተኛ የታማኝነት፣ የግልጽነት እና የፍትሃዊነት ደረጃን ይዞ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን።
የእኛ የቁጥጥር ማዕቀፍ ኢንቨስተሮችን ለመጠበቅ፣ መዋቅራዊ የአደጋ ስጋቶችን ለመቀነስ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን የሚያበረታታ ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋ እና ግልጽ የካፒታል ገበያ መኖሩን ለማረጋገጥ የተነደፈ ነው።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተቆጣጣሪ አካል እንደመሆናችን መጠን የየሰነደ ሙዓለ ንዋይ ልውውጦችን፣ የማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት እና ሁሉንም የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን የመቆጣጠር እና የመከታተል ኃላፊነት አለብን።
ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የመቆጣጠር አቅማችንን በማጎልበት በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ላይ ለሚፈጠሩ ተግዳሮቶች ፈጣን እና ውጤታማ ምላሽ እንድንሰጥ ያስችለናል።
በጠንካራ የቁጥጥር ሂደቶች
አማካኝነት ለሁሉም የገበያው ተሳታፊዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ አካባቢ ለመፍጠር እንሰራለን። እርስዎ ኢንቨስተር፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭ ወይም የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ቢሆኑ በገበያ ቦታ ላይ ፍትሃዊነትን፣ ግልጽነትን እና ታማኝነትን ለማረጋገጥ በእኛ ቁጥጥር ላይ መተማመን ይችላሉ።