የኢንቨስተር ዓይነት

ግባችን በእውቀት ላይ የተመሰረተ የኢንቨስትመንት ውሳኔ እንዲያደርጉ እና ፍትሃዊ እና ግልጽ የሆነ የኢንቨስትመንት ውሳኔ  እንዲያደርጉ በእውቀት ማብቃት ነው።

እያንዳንዱ ኢንቨስትመንት የአደጋ ስጋትን ይኖረዋል!

የኢካገባ ዓላማ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች በስርአት፣ በፍትሃዊነት፣ በቅልጥፍና እና ግልጽ በሆነ መንገድ የሚወጡበትና የሚገበያዩበት የካፒታል ገበያ ምህዳር መኖሩን ለማረጋገጥ ነው።

መደበኛ ኢንቨስተሮች፡

ይህ ምድብ ለትርፍ ዓላማ ሲል ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን የሚገዛ፣  የሚሸጥ ወይም የሚይዝን ማንኛውንም ሰው ያካተተ ነው።

ተቋማዊ ኢንቨስተሮች፣

በካፒታል ገበያ ምርቶች ላይ ኢንቨስት የሚያደርጉ ተቋማት/ኩባንያዎች ፣

    • ባንኮችን፣ ኢንሹራንሶችን፣ማይክሮ ፋይናንሶች፣ እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት፣
    • የፌዳራል እና የክልል መንግስታት፣
    • የጋራ ኢንቨስመንት ፈንዶች
    • የመንግስት የልማት ድርጅቶች
    • የጡረታ ፈንዶች ወይም አደረጃጀቶች

የውጭ አገር ኢንቬስተር

ማለት እንደ ኢትዮጵያዊ መቆጠር የሚፈልግ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ዜጋን ሳይጨምር በኢትዮጵያ ውስጥ የውጭ አገር ካፒታል በስራ ላይ ያዋለ ሆኖ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡-

    • የውጭ አገር ዜጋ፤
    • የውጭ አገር ዜጋ የባለቤትነት ድርሻ የያዘበት ድርጅት፤
    • ከኢትዮጵያ ውጭ በማንኛውም ኢንቬስተር የተመዘገበ ድርጅት፤
    • ከላይ በተጠቀሱት ኢንቬስተሮች በሁለቱ ወይም በሦሥቱ በጋራ የተቋቋመ ድርጅት፤
    • እንደ ውጭ አገር ኢንቬስተር መስተናገድ የመረጠ በቋሚነት በውጭ አገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ፤