በጠንካራ የገበያ ቁጥጥር እና ልማት የኢትዮጵያን የወደፊት የፋይናንስ አቅም ማጎልበት።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያዎችን የመቆጣጠር እና የካፒታል ገበያዎቹን እድገት እና ልማት የማበረታታት ኃላፊነት ያለበት ተቆጣጣሪ አካል ነው። በእርስዎ እና በእኛ ኃይል እናምናለን፣ እጅ ለእጅ በመሥራት የእርስዎን የዓመታት ጠንካራ ሥራ ወደ ቀላል፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ግልጽ ኢንቨስትመንት እናሳድጋለን።
አካታች ፋይናንስ ለጋራ ብልጽግና
በፈጠራ እና በቁጥጥር ልህቀት ፈር ቀዳጅ የካፒታል ገበያ ተቆጣጣሪ ለመሆን።
ፈጠራን እና የፋይናንስ አካታችነትን የሚያበረታታ እና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገትን የሚያመጣ የደመቀ የካፒታል ገበያ ስነ-ምህዳር ለማዳበር።
ኢካገባ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያዎች ቁጥጥር እና ልማት ውስጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። የእኛ ኃላፊነቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሰኔ 2013 ዓ.ም ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት ኤጀንሲ ሆኖ በይፋ ተቋቁሟል። አፈጣጠሩ/ አጀማመሩ የፋይናንሺያል ሴክተሩን / የፋይናንስ ዘርፉን ነፃ ለማድረግ እና የግል ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ያለመው የኢትዮጵያ ሰፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አካል ነበር። ኢ.ካ.ገ.ባ (ECMA) የተቋቋመው በአዋጅ ቁጥር 1248/2021 ሲሆን ይህም የአገሪቱን ታዳጊ የካፒታል ገበያ የመቆጣጠር ስልጣኑን ሕጋዊ መሠረት ይሰጠዋል። የኢ.ካ.ገ.ባ (ECMA) የመጀመሪያው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ባለሥልጣኑን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የመሩት ሲሆኑ ቆይታቸው መሠረታዊ የቁጥጥር ማዕቀፎችን በማዘጋጀት እና የካፒታል ገበያ ተቋማዊ አቅምን በማሳደግ ላይ ያተኮሩ ናቸው/ ነበሩ። በነሐሴ 2016 ዓ.ም ወ/ሪት ሃና ተኸልኩ/ቁ ሲተኳቸው በሕግ፣ በጠቅላላ ወንጀል ምርመራ እና በፋይናንሺያል ወንጀል ምርመራ ዕውቀትን በማምጣት አዲስ የተጠናከረ የቁጥጥር አፈፃፀም እና የገበያ ተዓማኒነትን አመላክተዋል።
የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ማዳበር እና ማጠናከር ስንቀጥል፣ ኢ.ካ.ገ.ባ (ECMA) ጠንካራ፣ ተቋቋሚ እና አካታች የፋይናንሺያል/ የፋይናንስ ሥርዓት የመገንባት ተልዕኮውን በቁርጠኝነት ይቀጥላል። የኢትዮጵያን የረዥም ጊዜ የኢኮኖሚ ግቦችን የሚደግፍ የበለፀገ የካፒታል ገበያ ራዕያችንን ለማሳካት ከአጋሮቻችን እና ከባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ ለመስራት በጉጉት እንጠብቃለን።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቦርድ አማካሪ
ጠበቃ እና የፋይናንስ አማካሪ (የቀድሞ AAU የአካዳሚክ ሰራተኞች)
ዋና ስራ አስፈፃሚ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ (ECX)
የፕሮግራም ዳይሬክተር፣ UNCDF
የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ለመቆጣጠር እና ለማልማት የተቋቋመ።
በፋይናንሺያል ሴክተር ውስጥ ግልፅነትን፣ ታማኝነትን እና እድገትን ማሳደግ።
በገበያ ተሳታፊዎች መካከል ፍትሐዊ አሠራርን እና ተገዢነትን ያረጋግጣል።
የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኢንቬስተሮችን ጥቅም ይጠብቃል።
የገበያ ቅልጥፍናን ለማሳደግ የፋይናንስ ፈጠራን ያበረታታል።
ለኢንቨስተሮች እና ባለድርሻ አካላት ግብዓቶችን እና ትምህርትን ይሰጣል።
የኢንቬስተር እምነትን ለማጎልበት ከዓለም አቀፍ መልካም ተሞክሮዎች ጋር ይጣጣማል።/ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ጋር በመጣጣም የኢንቨስተር እምነትን ያጎለብታል።