ECMA / ኢካገባ

አስደሳች ዜና ለኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ!

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን
ለአዋሽ ካፒታል አ.ማ. የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ በኢንቨስትመንት ባንክ (በባንክ ቡድን ውስጥ) ዘርፍ ሰጥቷል ።

ይህ በገበያው ልማት ውስጥ ሌላው ቁልፍ ምዕራፍ ሲሆን፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉት የተፈቀደላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ጠቅላላ ቁጥር ወደ አስራ ሦስት (13) እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮች ጠቅላላ ቁጥር ወደ አራት (4) ከፍ አድርጓል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ ፈቃዱን ያስረከቡ ሲሆን ለአዋሽ ካፒታል አምስት (5) የቦርድ አባላት ሹመት እና አራት (4) ተሿሚ እንደራሴዎች መጽደቅ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ይህ አዲስ ሁነት በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ላይ እያደገ ያለውን እምነት የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ የባለሥልጣኑን ዘላቂ ዕድገትን እና ባለሀብቶች ጥበቃን የሚደግፍ ተወዳዳሪ፣ ፍትሃዊ እና ጠንካራ ገበያ ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት ያጠናክራል።