ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQs)

ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQs)

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የቁጥጥር ሳንድቦክስ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያዎች ባለስልጣን (ECMA) የተቋቋመ ማዕቀፍ ሲሆን የንግድ ድርጅቶች አዳዲስ የካፒታል ገበያ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ቁጥጥር በሚደረግበት አካባቢ ውስጥ እንዲሞክሩ ያስችላቸዋል። ይህም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ወደ ሰፊው ገበያ ከመድረሳቸው በፊት ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ጠቃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይረዳል።

ሳንድቦክሱ የሚከተሉትን ጨምሮ ለተለያዩ ድርጅቶች ክፍት ነው።

  1. አዳዲስ ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ ፈቃድ ያላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት አቅራቢዎች።
  2. ቁጥጥር በሚፈልጉ ተግባራት ላይ ለመሰማራት የሚያቅዱ ፈቃድ የሌላቸው ድርጅቶች።
  3. በአሁኑ ጊዜ ቁጥጥር የማይደረግባቸው፣ ነገር ግን ወደፊት ቁጥጥር ሊያስፈልጋቸው የሚችሉ እንቅስቃሴዎችን የሚያቀርቡ ድርጅቶች።
  4. የካፒታል ገበያን የሚደግፉ ነገር ግን ራሳቸው ፈቃድ የማያስፈልጋቸው የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች።
  5. የቁጥጥር ተግባራትን ለማሻሻል ቴክኖሎጂዎችን (SupTech) በመገንባት ላይ ያሉ ድርጅቶች።

ተሳታፊዎች አነስ በሚሉ የቁጥጥር እንቅፋቶች/ማእቀፎች ምርቶቻቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ መሞከር፣ ከተቆጣጠሪዎች የተበጀ ምክር እና መመሪያን መቀበል፣ ከባለድርሻ አካላት ተአማኒነትን ማግኘት እና ለገበያ ለመቅረብ የሚወስድባቸውን ጊዜ ማፋጠን ይችላሉ። ተሳትፎው ለሙከራ እና ለልማት አስፈላጊ የሆኑ ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን እና የመረጃ ቋቶችን ያቀርባል። ይህ ፕሮግራም ለተሳታፊዎች የገንዘብ ድጋፍ እንደማይሰጥ ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ነው።

ፍላጎት ያላቸው ወገኖች በመጀመሪያ ከሳንድቦክሱ ቡድን ጋር በመወያየት ሃሳባቸውን መወያየት አለባቸው። ተስማሚ ሆኖ ከተገኘ በተዘጋጀው የኦንላይን መድረክ በኩል ዝርዝር ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ። ማመልከቻዎች የሚገመገሙት አስቀድሞ በተገለጸው የብቃት መስፈርት መሰረት ነው፣ እናም የተሳካላቸው አመልካቾች የሙከራ እቅድ ለማውጣት እና ለማስፈጸም ከተቆጣጠሪዎች ጋር ይተባበራሉ/አብረው ይሰራሉ።

የሚሰጠው ድጋፍ የሚከተሉትን ያካትታል:-

  • የሙከራውን ወሰን እና ሁኔታዎች የሚገልጹ የሙከራ ማጽደቂያ ደብዳቤዎችን (TALs) መሞከር።
  • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የተሻሻሉ የፍቃድ አሰጣጥ ዝግጅቶች።
  • ጊዜያዊ የህግ ተፈጻሚነት የሚቀርባቸው ሁኔታዎች ወይም ማሻሻያዎች።
  • የቁጥጥር ተገዢነትን በተመለከተ የግለሰብ ምክር እና መመሪያ።
  • አስፈላጊ ከሆነ ወደ አስፈላጊ የመረጃ ቋቶች እና መሠረተ ልማት መድረስ።

ሳንድቦክሱ ለሁሉም የፋይናንስ ፈጠራዎች ክፍት ቢሆንም፣ በተለይም የፋይናንስ አካታችነትን በእጅጉ የሚያሻሽሉ፣ የሸማቾች ጥበቃን የሚያሻሽሉ፣ ክፍያዎችን የሚያመቻቹ ወይም አጠቃላይ የፋይናንስ መሠረተ ልማቶችን በኢትዮጵያ የሚያጠናክሩ ቴክኖሎጂዎችን በደስታ ይቀበላል።

የሙከራው ደረጃ እስከ 12 ወራት ሊቆይ ይችላል፣ ነገር ግን የቆይታ ጊዜው እንደ ፕሮጀክቱ ልዩ ፍላጎቶች እና እንደ መጀመሪያዎቹ የሙከራ ወቅቶች ውጤቶች ሊለያይ ይችላል።

የሙከራ ወቅቱ ሲጠናቀቅ ተሳታፊዎች ስለ ግኝታቸው እና ውጤቶቻቸው ዝርዝር ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በዚህ ሪፖርት ላይ በመመስረት የምርቱን ወይም የአገልግሎቱን የወደፊት ሁኔታ በሚመለከት (ወደ ሙሉ ገበያ ማሰማራት መሸጋገር፣ ተጨማሪ ሙከራ፣ ወይም ስራው መቆም አለበት በሚለው ዙሪያ) ውሳኔ ይወሰዳል።