በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ቁጥጥር ሳንድቦክስ ውስጥ መሳተፍ ለድርጅቶች ልዩ የሆነ የቁጥጥር ድጋፍ፣ ምክር እና ስልታዊ ጥቅሞችን ያስገኛል። እነዚህም አዳዲስ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ለመሞከር እና ለማልማት ታስበው የተነደፉ ናቸው።
ወደ ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ የቁጥጥር ሳንድቦክስ የገባ እያንዳንዱ ድርጅት ልዩ የሆነ የቁጥጥር ማዕቀፎችን እና ድጋፍን የሚፈልግ አዲስ ፈጠራን ያመጣል። ይህንን በመገንዘብ ሳንድቦክሱ ለግል የተበጀ የቁጥጥር ዕርዳታን፣ ስልታዊ ምክርን እና ቀጥተኛ ጥቅማ ጥቅሞችን ያቀርባል። እነዚህም በካፒታል ገበያው አዳዲስ ፈጠራ የሆኑ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ውጤታማ ሙከራ እና ልማትን ለማመቻቸት ነው።
ሳንድቦክሱ ለተሳታፊዎች ልዩ ፍላጎቶች የተበጁ የቁጥጥር መሣሪያዎች ስብስብ ያቀርባል፣ ይህም ተገዢነትን እና የሸማቾች ጥበቃን በማረጋገጥ ውጤታማ ሙከራን ያስችላል። ተቆጣጣሪዎቹ ተሳታፊዎቹ ሙከራዎችን እንዲያከናውኑ በሚያስፈልጋቸው ድጋፍ መሠረት ከግምገማ በኋላ ለእያንዳንዱ ጉዳይ ራሱን የቻለ የቁጥጥር ድጋፍ ይሰጣሉ።
የሙከራ ማረጋገጫ ደብዳቤዎች (TALs) በሙከራ ወቅት መጀመሪያ ላይ ለተሳታፊዎች ይሰጣሉ፣ የሙከራውን ወሰን፣ ሁኔታዎች እና የቆይታ ጊዜ ይገልፃሉ። የማረጋገጫ ደብዳቤዎቹ ድርጅቱ በተወሰኑ ሁኔታዎች ሙከራዎችን እንዲያካሂድ እንደተፈቀደለት ከECMA መደበኛ ዕውቅና ይሰጣሉ።
የሳንድቦክሱ ተሳታፊዎች የቁጥጥር ማዕቀፎችን ፣ የተገዥነት ግዴታዎችን እና የአደጋ ስጋት አስተዳደርን መሻገር በሚችሉባቸው መንገዶች ዙርያ የተበጁ ምክሮችን ያገኛሉ። ይህም ማክበር የሚጠበቁባቸውን የቁጥጥር ደንቦች በሙከራ ሂደት ውስጥ እንዲገነዘቡ ያስችላል። ከማተሪያው/ሳንድቦክሱ ተቆጣጣሪዎች ጋር ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የሚያደርጉት መደበኛ ያልሆነ መስተጋብር ስለ ቁጥጥር ጉዳዮች ለድርጅቶች ፈጣን እና ተግባራዊ ግንዛቤዎችን ያስጨብጣሉ ፣ ይህም አሠራሮቻቸውን እና ስልቶቻቸውን በፍጥነት የማስተካከል ችሎታቸውን ያሳድጋል።
ECMA ከተፈቀደላቸው ድርጅቶች ጋር በመተባበር የቁጥጥር ድጋፍን ይሰጣል፣ ይህም የፈጠራዎች እንከን የለሽ ሙከራን ያመቻቻል። ሳንድቦክሱ አሁን ካሉ የፈቃድ አሰጣጥ ማዕቀፎች ጋር ሙሉ ለሙሉ የማይጣጣሙ ፈጠራዎችን ጭምር ያስተናግዳል። አሁን ያሉት የቁጥጥር ማዕቀፎች የፈጠራ ሙከራን ሊያደናቅፉ በሚችሉበት ጊዜ ሳንድቦክሱ ተለዋዋጭነት ይሰጣል፣ ይህም ኩባንያዎች ሙሉ የቁጥጥር ተገዢነት ሸክም ሳይኖራቸው አዳዲስ መፍትሄዎችን እንዲሞክሩ ያስችላቸዋል።